Saturday, August 24, 2013

ሰዎች ሁሉ በሕግ ፊት እኩል አይደሉም!!!


ሰዎች ሁሉ በሕግ ፊት እኩል አይደሉም!!!


አቶ ወረታው ዋሴ (የሰማያዊ ፓርቲ ጥናትና ስትራቴጂ ኃላፊ)

አሁን አሁን ሕገ-መንግስቱ በተግባር ሲመዘን የተፃፈበትን ቀለምና ወረቀት ያህል 

እንኳ ዋጋ የለውም የሚለው አባባል እውን እየሆነ የመጣ ይመስላል፡፡ መቸም 

ገዥዎች እንደፈለገ መቀለጃ ቢደርጉትም ይሔው ሕገ-መንግስት ሰዎች ሁል በሕግ 

ፊት እኩል ናቸው ይላል፡፡ ሰው ማለት የተፈጥሮ ሰውና በሕግ እወቅና ያገኘ ሊከስና 

ሊከሰስ የሚችል አካልን ያካትታል፡፡ እናማ ሕግን እናስከብራለን የሚሉ የፀጥታና 

የደህንነትኃይሎች ኢህአዲግ የሚባለው አካል በየትም ቦታ ቢሰበሰብ፣ በየትም ቦታ 

ቢቀሰቅስ ወይም በየትም ቦታ መንገድ ቢዘጋ አይጠይቁም፤ መጠየቅም አለበት 

ብለው አያምኑም፡፡ ምክንያቱም ለእነሱ ሰው ሁሉ በሕግ ፊት እኩል አይደለም፡፡ 

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም ሌሎች የሲቪክ ማህበራት የአደባባይ ስብሰባ ወይም 

ሰልፍ ማድረግ ቢፈልጉ ማሳወቅ ግዴታቸው ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ይሕንንም 

በጡንቻም ጭምር ያስፈፅማሉ፡፡ ይህ ግዴታ ግን ገዥውን ቡድን አይመለከትም፡፡ 

ስለዚህም የፀጥታና የደሕንነት ኃይሎቻችን አይጠይቁም፤ ትንፍሽም አይሉም፡፡ 

ይህንንም ለማረጋገጥ የሰማያዊ ፓርቲ የሰልፍ አስተባባሪ አባላት በዛሬው ዕለት 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ኃላፊ ጋር ባደረጉት 

ውይይት የኢሕዲግ አባላት የመለስን የሙት ዓመት አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ 

ያደረጉትን ኃዘን ይሁን ዳንኪራ ለመለየት አስቸጋሪ የሆነ ዝግጅት ከማድረጋቸው 

በፊት በሕጉ መሰረት ለሚመለከተው አካል ያላሳወቁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ 

ለፋሽቱን ግራዚያኒ መታሰቢያ ሐውልትና በስሙ የመናፈሻ ቦታ መሰራቱን 

በመቃወም ሰልፍ በመጥራታችንና ሕዝብም በሰልፉ ላይ እንዲሳተፍ ለመቀስቀስ 

ስንዘዋወር የፀጥታና የደሕንነት ኃይሎች “ፈቃድ” አምጡ በማለት ስራችንን 

ከማደናቀፋቸውም በላይ እጅግ ጸያፍ በሆኑ ቃላት ሰብዕናችንን በማርከሰና ወደ 

እስር ቤትም በመወርወር ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመውብናል፡፡ ከዚህም በኋላ የሰማያዊ 

ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም የተቃዉሞ ሰልፍ ለማድረግ ሕዝብን 

ለመቀስቀስ በወጡ አባላቱ ላይ ከፍተኛ እንግልት፣ ወከባና እስራት ደርሶባቸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ምነው እኛ ላይ 

እንደሚያደርጉት የኢሕአዲግ አባላት ያልተፈቀደ የአደባባይ ስብሰባ ሲያደርጉ 

እንደለመዱት ለፖሊስና ለደሕንነት በመፃፍ ለምን አላስቆሟቸውም? እናንተ የፀጥታ 

ኃይሎችስ ሕግ የሚሰራዉ ለተቃዋሚ ፓርቲ ብቻ ይመስላችኋልን

No comments: