Friday, August 30, 2013

‹‹አክራሪነትን አዎ እናወግዛለን!››

‹‹አክራሪነትን አዎ እናወግዛለን!››፣ ‹‹በአክራሪነት ሽፋን ግን በእምነታችን ጣልቃ 

መግባትንም በተመሳሳይ እናወግዛለን›› ልንል ወደ ሰልፉ እንተማለን፡፡ በሰልፉ ላይ 

በመገኘት መንግስት ሰልፉን ከተቀመጠለት ስያሜ ውጪ ለህገ ወጥ ተግባሩና 

ፖለቲካዊ ትርፍ ማጋበዣው መጠቀሚያ እንዳያደርገው እናደርጋለን፡፡ 

ሃላፊነት በጎደለውና ከልክ ባለፈ ንቀት የሙስሊሙን እምነት ለመበረዝ ሲሞክርና 


አማኙን በማንገላታት ለመፍጠር የታለመው ሀገራዊ ትርምስ አልሳካ ሲል ዛሬ 

አሰላለፍን በመቀየር በሃይማኖቶች ሽፋን ህዝብን በህዝብ ላይ ለማነሳሳት የተቀመረ 

ስሌት ካለ እንደማይሳካ የፊታችን እሁድ በተግባር እናስመሰክራለን፡፡ ይህን ክፉ ራዕይ


ዳግም መና ለማስቀረት ዛሬም ከሃገር ወንድምና እህቶቻችን ጋር 

እምነትና አስተሳሰብ ሳይለየን እጅ ለእጅ በመያያዝ ለዘመናት በገዢዎች ያልተናደውን 

አንድነታችንን እናጠናክራለን፡፡

#የነሃሴ 26 ሰልፍን ስንሳተፍ አክራሪነትን በመቃወም እና አብሮነትና ተቻችሎ 


መኖርን በተግባር እናሰይበታለን፡፡ ሆኖም አክራሪነትን ከመቃወም ውጭ በሰልፉ ላይ 

የሚስተናገዱ ማንኛውንም አይነት አፍራሽ መርሃ ግብሮች ካሉ በፅኑ እናወግዛለን፡፡ 

ሁሌም ደጋግመን ስንገልጸው እንደነበረው ሁሉ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ጥያቄም ሆነ

እንቅስቃሴ ሰላማዊ፣ አገራዊ እና ህዝባዊ መሆኑን እንዲሁም ይምነት እንጂ የፖለቲካ 

ጉዳይ አለመሆኑን እና ከመብት እና የፍትህ ጥያቄ ውጭ የተለየ መልክ እና ይዘት 

እንደሌለው ለሁሉም ኢትዮጵያውያን አሁንም ደግመን ማስረገጥ እንሻለን:: 

በመሆኑም ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በሙሉ ከእነ ቤተሰቡ ነቅሎ በመውጣት በእሁዱ 

የተቃውሞ መርሐ ግብር ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ ተላልፏል፡፡ ሁላችንም እዛው 

እንገናኛለን፡፡ ለእለቱ ከሚቀመጠው መርሐግብር ክንውን ሳንላቀቀ የተቀመጠውን 

ብቻ በመፈጸም አክራሪነትን ከሌሎች ኢትዮጵያውን እህቶችና ወንድሞች ጋር 

በመሆን በተግባር እናወግዛለን፡፡

የእለቱን የመርሐግብር አፈጻጸም

አስመልክቶ በቀጣዩ ፖስት ላይ ይመልከቱ፡

አላሁ አክበር!

From #DY

No comments: