Friday, August 30, 2013

የነሀሴ 26 መርሐግብር አፈጻጸም በተመለከተ

የነሀሴ 26 መርሐግብር አፈጻጸም በተመለከተ

በዕለቱ መደበኛውን የሰልፍ መርሃግብር ሙሉ በሙሉ በቋሚነት የምንከተል ሲሆን 

በተጨማሪ ግን:

* ሁሉም የሃይማኖት አባቶች ሰላምን፣ፍቅርን እና መቻቻልን እንደሚሰብኩ፣

እኩይ ተግባራትን እና አክራሪነትን እንደሚቃወሙና የሰላም እንደራሴዎች እንደሆኑ 

ለማሳየት እንዲሁም የሃይማኖት አባቶቹ ለወከሉት እምነትና በእምነቱ ስር ላሉ

አማኞች ያለንን ክብር ለማሳየት ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት የማናምንበትን ወይም 

ሞራላችንን የሚነካ ንግግር ቢያደርጉ እንኳ በጥሞና ንግግራቸውን እናደምጣለን፡፡

በምንም መልኩ የሃይማኖት አባቶቹ ንግግር ሲያደርጉ ንግግራቸው እንዲቋረጥ 

አናደርግም፡፡ ንግግራቸውን እንዳጠናቀቁም የሰላም መገለጫ የሆነ ነጭ ነገር

እናውለበልባለን፡፡ ለዚህም መሃረብ፣ ነጭ ወረቀት፣ ሶፍት እና መሰል ቀላል ነገሮችን 

መጠቀም እንችላለን፡፡

* ህዝብ በይፋ ባወረደው ህገ-ወጥ የቀበሌ ሹመት የመጡ የመጅሊስ ሹመኞች 


ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ንግግራቸውን እስኪጨርሱ ያለምንም ድምፅ  

ሁለቱንም ጆሯችንን በመዳፋችን ደፍነን እንቆያለን፡፡

* ንግግር የሚያደርጉ የመንግስት ባለስልጣናት ካሉ በሚሊዮኖች ፊርማ

የወከልናቸው ኮሚቴዎቻችንን በማሰር መላውን መብት ጠያቂ ህዝበ ሙስሊም ያሰሩ 

መሆናቸውን ለመግለጽና የነጠቁንን መብታችንን በመመለስ ሕዝቡን ከእስራት 

እንዲፈቱት ለመጠየቅ ንግግራቸውን እስኪጨርሱ ያለምንም ድምፅ ሁለት እጃችንን 

ወደላይ ከፍ አድርጎ በማንሳትና በማጠላለፍ ምልክት ብቻ እናሳያለን

No comments: