Friday, August 9, 2013

40 የዓድዋ ተወላጆች ታሰሩ

40 የዓድዋ ተወላጆች ታሰሩ


ከዓመታት በፊት በእርሻ መሬት ማነስ ምክንያት ወደ 400 የሚሆኑ የዓድዋ 

ተወላጆች (ልዩ ስሙ ‘ወርዒለኸ’ ከሚባል ቦታ) በመንግስት አካላት ከቀያቸው 

ተነስተው በቃፍታ ሑመራ ወረዳ (ጣብያ ማይወይኒ፣ ቁሸት መንሼን)እንዲሰፍሩ 

ተደረገ። ቤት ሰሩ፤ ኑሯቸው እዛው መሰረቱ።

አሁን ግን አዲስ ነገር ተከሰተ። የሰፈሩበት፣ ኑሯቸው የመሰረቱበት መንደር ለከብቶች 


እርባታ ‘ተስማሚ ሁኖ ስለተገኘ’ በኢንቨስትመንት ስም ከብቶች ለሚያረባ ድርጅት 

እንዲሰጥ ተወሰነ። አርሶአደሮቹ ያለ ምንም ካሳ ቀያቸው ለቀው እንዲነሱ ታዘዙ። 

ካሳ ጠየቁ፤እንደማይሰጣቸው ተነገራቸው። ለመኖርያ የሚሆን ቅያሪ ቦታ ጠየቁ። 

መልስ አልተሰጣቸውም። ቀያቸው ባጭር ግዜ ዉስጥ ለቀው እንዲወጡ ሲነገራቸው 

አርሶአደሮቹ ጠንከር ያለ ተቃውሞ አሰሙ።

ከነዚህ 400 የሚሆኑ የተፈናቀሉ አርሶአደሮች ‘የተቃውሞው አስተባባሪዎች ናቸው’ 


ተብለው የተጠረጠሩ 40 አባወራዎች ታሰሩ። ክስ መመስረት እንኳን አይችሉም። 

ምክንያቱም መሬት የመንግስት ነው።

መሬት የሌለው ዜጋ ሀገር የለውም። መሬት የመንግስት

ከሆነ የመንግስት አካላት (የገዢው ፓርቲ አባላት) በፈለጉበት ግዜ ዜጎችን ማፈናቀል 

ይችላሉ።ለትግራይ ተወላጆች በሙሉ …….


Abraha Desta

No comments: