Monday, August 5, 2013

የኢሃዴግ መንግስት ‪EPRDF‬ ሰብአዊ መብት አያያዝ

የኢሃዴግ መንግስት EPRDF‬ ሰብአዊ መብት አያያዝ ‪‎Humanrights‬ በመጀመሪያዎቹ አስር የስልጣኑ አመታት ይበልጥ አስከፌ ነበር፡፡ በቅርብ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ሪፓርቶችን ሳገላብጥ እንዳየሁት ፣ የሰዎች መሰወር፣ የመንገድ ላይ ግድያ፣ የጋዜጠኞ መታሰርና መገረፍ የሚዲያ ተቋምት በተደጋጋሚ መዘጋት(ከነችግራቸው) የሰላማዊ ሰልፍ እና ያልታጠቁ ሰዎችን ተቃውሞ ለማደናቀፍ መተኮስ ሪፓርቶች ውስጥ ተደጋጋሚ የሚጠቀሱ ነበሩ፡፡ እነዚህ የመብት ጥሰቶች በወቅቱ በተለያዩ ተቋማት በብዙ ተጽእኖ ውስጥ ሆነውም ሪፓርት ይደረጉ ነበር፡፡ከዘጠናዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ግን ቢያንስ የተጠና እና ሲስተማቲክ ጭቆና ካልሆነ በስተቀር እንደዱርየ መንገድ ላይ መታኮስን አቁመዋል፡፡ በተወሰነ መልኩም ወደልማት ስራ ፌታቸውን አዙረዋል ብየ አስብ ነበር፡፡ በተለይ በከተሞች አካባቢ፡፡ በሰፌው ሰው የተገደለበት የምርጫ 97ት ግድያ ውጪ በቅርቡ የሚጠቀስ የመንገድ ላይ ግድያ አልነበረንም፡፡

አርብ እለት አርሲ ኮፈሌ ላይ ተፈጠረ የተባለውን ሪፓርት ተከትሎ ይህንን ሃሳቤን በድ ጋሚ እየከለስኩ ነበር፡፡ ኢህአዴግ ተሸሽሎ ነው ወይስ በሲስተም ጸጥ ማሰኘቱ ረድቶት መንገድ ላይ መተኮስ ያቆመው? ጠፍረው የሚይዙት ህጎች ባይኖሩ ኖሮ ሲቪል ተቃውሞን የሚያሰሙ ሰዎችን የሚያስተናድበት መንገድ ከ1983 ልዩነቱ ምንድነው? ከ22 አመት የመንግስትነት ቆይታም በሁዋላ መስኪድ ውስጥ የሚተኩስ መንግስት ነው ወይ ያለን ? ለዚህ ተጠያቂው ማነው? ያልታጠቁ ሰዎች ላይ እንዴት ተኩስ ይከፈታል? ( የፈለገ አለመስማማት ቢኖር) ሲጀመር ወታደር ምን ሊያደርግ መስኪድ ይገባል ? ገለልተኛ መረጃ ከማን እናግኝ ? ሲቪል ሶሳይቲ ተቋም የለን! ሚዲያ የለን! ሰብአዊ መብት ተቋማት የሉን……ያለን ኢህአዴግና ወታደሮቹ ናቸው፡፡ (ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ለምትችሉ ሰዎች ዘመዶች የምታውቁት ሰው ….ያላችሁ ትብብራሁን እለምናለሁ)

ከሁለት አስርት በላይ መንግስት ሆኖ ቆይቶ አሁንም የእምነት ቦታ የሚተኩስ መንግስትን ለማመን ሁሉ ከባድ ነው፡፡ አሸባሪዎችም ካሉ በየእምነት ቦታው ከሚታኮሱ ለምን ህጉን ለእንዲህ አይነቱ ቦታ ተግባራዊ አይደርጉትም??

What has been done in Kofele ‪‎Arsi‬ ‪‎Oromiya‬ is outrageous and irresponsible. If I keep silent on this፣ then I will not have a moral right to talk about other rights violation. So I speak. No for ‪#‎injustice‬! No for killing!

https://www.youtube.com/watch?v=665UHkCRdiQ


No comments: