Sunday, August 11, 2013

ኢህአዴግ ሲፈልግና ሳይፈልግ

ኢህአዴግ ሲፈልግና ሳይፈልግ
ከፈለገ --- በትምህርት ቤት አዳራሽ 
ስብሰባ ያደርጋል
ካልፈለገ--- ትምህርት ቤት ውስጥ 
የፖለቲካ ስብሰባ አይደረግም በማለት 
ይከለክላል
ከፈለገ ---ትምህርት ቤቶችን እስር ቤት 
ያደርጋል
ካልፈለገ -- ሼሁን የገደሉ በማለት ስለ 
አንድ ሰው ሞት ወገቡን ገትሮ ይከራከራል
ከፈለገ -- በቤ/ክ አውደ ምህረት የሃይማኖት መምህር ሲገደሉ እንዳላየ ይሆናል
ከፈለገ -- ተቃዋሚዎችን በህገ መንግስት ጥሰት ይከሳል
ካልፈለገ-- ህገ መንግስቱን በአደባባይ ይደፈጥጣል
ከፈለገ -- ሰላማዊ ሰልፍ አድርጉ ይላል
ካልፈለገ -- ለሰላማዊ ሰልፉ ህዝብ መቀስቀስ አይቻልም ይላል
ሲነሽጠው -- ምርጫውን ፍጹም ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ ቆርጬ ተነስቻለሁ 
ይላል
ካልፈለገ -- የምርጫ ክርክር በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት አይተላለፍም ይላል
ከፈለገ --- ባንዲራ ጨርቅ ነው ይላል
ካልፈለገ---በባንዲራው መለስን ከፍኖ ይቀብርና የተቀደደ ባንዲራ እንዴት 
ታውለበልባላችሁ ይላል
ካልፈለገ-- ሱዳን ሄዶ የተዘቀዘቀ ባንዲራ ያውለበልባል
ከፈለገ -- አህባሽን ተከተሉ ይላል
ካልፈለገ--ሲደራደራቸው የከረሙ ሰዎችን ሽብርተኞች በማለት ዘብጥያ ያወርዳል
ከፈለገ --- የግል ቴሌቭዥን እፈቅዳለሁ ይላል
ካልፈለገ -- በሞንታርቦ መቀስቀስ አይቻልም ይላል፡፡ኢህአዴግ ሲፈልግና 
ሳይፈልግ 
እኛ እስከ መቼ እንናጥ ይሆን?

No comments: