Saturday, August 10, 2013

የሰላማዊ ትግል ምንነት

”የሰላማዊ ትግል ምንነት ለማይረዱ ትልቅ ትምህርት የሰጠ፣ ኢህአዴግ ፍጹም የሆነ 

ልምድ ባካበተበትና ኤክስፐርት በሆነባቸው የትግል ስልቶች ብልጫ ወስዶ 

ለማንበርከክ እንደሚያስቸግር፣ ሰላማዊ ትግል ከራስና ከስሜት ጋር የሚደረግ ታላቅ 

አስተምህሮት መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል። የድምጻችን ይሰማ ትግል በዚህ መልኩ 

በኢትዮጵያ ቀዳሚ ሆኖ ይቆያል” በግል አድራሻ ከተላከ አስተያየት የተወሰደ።

በአሃዝ፣ ጉዳቱ በሚገለጽበት መጠን፣ ጉዳቱ የሚገለጽበት ደረጃና የቋንቋው አቅም 


ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ወገኖች፣ የውጪ ታዛቢዎች፣ በቀጥታም ይሁን 

በተዘዋዋሪ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት፣ ራሱ ኢህአዴግ፣ ህወሃትና መላው 

ወዳጆቹ በአንድ እውነት ይስማማሉ። እሱም ህወሃት ራሱ ባመጣው ጣጣ፣ ራሱ 

ትዕዛዝ ሰጪ ሆኖ ያደረሰው ሰብአዊና በቀላሉ ሊበርድ የማይችል መከራ እንደሆነ 

በየአቅጣጫው አስተያየት እየተሰጠ ነው።

No comments: