Tuesday, August 6, 2013

የሬዲዮ ቢላል ጋዜጠኞች ታሰሩ የት እንደደረሱ አልታወቀም

ሰሞኑን የሙስሊሞችን ጉዳይ አስመልክቶ የመከላከያ ሰራዊት በህዝበ ሙስሊሙ ላይ 

ከፍተኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ይታወሳል ።ይህንን ጉዳይ አያይዞ ደግሞ 

የቢላል ሬዲዮ ጋዜጠኞችን አፍኖ በመውሰድ የት እንዳደረሳቸው አልታወቀም 

ከአራት ጋዜጠኞች በላይ የደረሱበት አለመታወቁ የኢትዮጵያ መንግስት በፕሬሱ ላይ 

የሚያደርገውን ጫና ምን ያህል የከፋ እንደሆነ ያሳያል በተለይም በአፍሪካ የፕረስ 

ነጻነት የተሰኘው አጠቃላይ የአፍሪካ ጋዜጠኞች በሚሳተፉበት ስብሰባ ላይ አዘጋጅ 

ሃገሯ ኢትዮጵያ መሆኗ አከራካሪ ሆኖ ቀርቧል። የፕረስ ነጻነትን ለአፍሪካ የሚለው 

ጉዳይ ኢትዮጵያን እና ኤርትራን ሊያካትት አይገባም ያሉት የተለያዩ አፍሪካ ሃገራት 

ፕሮፌሰሮች እና የሚዲያ አካላቶች በመጨረሻ ላይ ግን በአዲስ አበባ ላይ እንዲደረግ 

ከድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን እና አዲስ አበባ ልትመረጥበት የቻለችበት ምክንያት 

የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ መዲና መሆኗ ነው ሲሉ አክለው የገለጹ ሲሆን ከፕረስ 

ነጻነት ጋር ምንም የማያገናኘውን ሃሳብ ማቅረባቸው የአፍሪካ ምሁራንን ሊያስወቅስ 

ችሏል። የፕረስ ነጻነትን በሚያከብሩ ሃገራት ላይ ቢደረግ ለሌሎችም አርአያ እንዲሆኖ ሰርቶ ማሳያ መሆን ሲገባ አፈና በምታበዛው ኢትዮጵያ ላይ ይህንን 

ማድረጉ ተገቢ አለመሆኑን ብዙሃኖች የሚቃወሙት ቢሆንም አስተባባሪው ኮሚቴ 

ግን በኢትዮጵያ እንዲደረግ መወሰኑ የሚያሳፍር ተግባር ነው። በተለያዩ ቦታዎች 

ወከባ ድብደባ እና ግድያ በበዛበት ሰሞን ጋዜጠኞችን ምንም ወደማያውቁት ቦታ 

መወሰዳቸው እና ምንም አመላካች ነገር ባለያዘበት በዚህ ወቅት መንግስት በህዝበ 

ሙስሊሙ በሚያደርገው ሰላማዊ ጥያቄ ከፍተኛ ፍራቻ ውስጥ እንደገባ እና ለዚህም 

መቀጣጫ ብሎ የወሰነውን እርምጃ በሰላማዊው ህዝብ ላይ በተረጋጋ መንፈስ 

ህብረተሰቡን እያጠቃ መሆኑን ከሃገር ቤት የደረሰን መረጃ ያመለክታል በተለይም 

በዚህ ረመዳን ጾም ወቅት ምንም ክፋት ነገር የማድረግ ፍላጎት የሌለው እና 

ትኩረቱን ለረመዳን ጾም ያደረገውን ህዝበ ሙስሊሙን የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ 

ድብደባ እና ግድያ እያደረገ ቁጥራቸው ከሃያ የሚበልጡ ህዝበ ሙስሊሞች በተለያዩ 

ቦታዎች መገደላቸው የሰሞንኛ ዜና እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የተለያዩ ሚዲያዎች 

እንደዘገቡት የሚታወቅ ነው ።ሆኖም ግን አሁንም በዚህ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት 

አላርፍም ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ህብረተሰቡን ሰላም እየነሳ መሆኑን ብዙሃኖች 

ይጠቁማሉ ።በዚህ በሚቀጥሉት ቀናትም በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የፍርድ 

ሁኔታም የሚታይበት ቀን በመሆኑ ህዝቡ በፍርድ ቤት ተገኝቶ የፍትህን መንገድ 

አብሮ ከደሳለኝ ጋር እንዲከታተሉ ሲሉ አንዳድን የፖለቲካ ድርጅቶች ይጠቁማሉ 

፣የአንድ ሰው መብት መጣስ የህዝብን መብት መጣስን የሚያሳይ ሲሆን ህግ

ስርአቱን ይዞ የማይጓዝ እና ለገዢው የሚያደላ ከሆነ ደግሞ የፍትህን መጓደል 

ያሳያል ስለዚህ ለፍትህ በጋራ እንቁም ሲሉ ገልጸዋል ።በተያያዘም ዜና የሙስሊሞች 

ጉዳይ ኮለመኒስት የነበረው ጋዜጠኛ ካህሊድ ሙሃመድ እስካሁን የደረሰበትም 

አይታወቅም ።8/6/13 የሬዲዮ ቢላል ጋዜጠኞች ታሰሩ የት እንደደረሱ አልታወቀም


Yihune Abyssinia Ephrem

No comments: