Saturday, August 10, 2013

ሀገራዊ ጥሪ

                    ሀገራዊ ጥሪ

     የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል

የወያኔን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድየግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይልበሃገር ወዳድና ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች፣ ምሁራን እና በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተደራጀ ኃይል ነው።
በአሁኑ ወቅት አያሌ ኢትዮጵያዉያን ወያኔን ለመታገል መሳሪያ ካነሱ ከነጻነት ታጋዮች ጋር በየቀኑ እየተቀላቀሉ ናቸው፡፡ ትግሉን የበለጠ ለማጠናከር እና የአምባገነኑን ስርአት ውድቀት ለማፋጠን ወገኖቻችን ተማሪዎች፤ ገበሬዎች፤ነጋዴዎች፤ ላብ አደሮች፤ በመንግስት ሴክተሩ እና በሌሎች ተቋማት የምትገኙ ሁሉ  ግንቦት 7 ሕዝባዊ ይልን እንደሁሌ  የውስጥ አርበኛ በመሆ የነጻነት ትግሉን በመቀላቀል፣ ራሳችሁንና ሀገራችሁ ከወያኔ የዘረኛ ገዛዝ መዳፍ እጅ ነጻ ትወጣ ዘንድ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ የአባቶቻችንን አኩሪ ታሪክ ለመድገም ትግሉን በመቀላቀል ፍርሃታችሁን ጣጥሳችሁ በመደራጀት የዜግነት ግዴታችሁን እንድትወጡ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ይል ጥሪውን ያቀርባል።
ተባብረን ወያኔን እናስወግድ!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!







No comments: