Friday, August 9, 2013

በትላትናው በኢድ በአል ቀን በመንግስት ታጣቂዎች በህዝበ ሙስሊሙ ላይ በተፈፀመው የሽብር ጥቃት የጥቃቱ ሰለባ ከመሆንም አልፎ ታስረው የነበሩት ሙስሊሞች እየተፈቱ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በትላትናው እለት በኢድ አል ፊጥር በአል ላይ የኢድ ሰላት መጠናቀቁን ተከትሎ ህዝበ ሙስሊሙ ሰላማዊ ተቃውሞውን አሰምቶ ወደየቤቱ በመመለስ ላይ በነበረበት ወቅት የመንስግት ታጣቂ ሃይሎች ባደረሱት የሽብር ጥቃት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሙስሊሞች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው የሚታወስ ነው፡፡

የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች በፈፀሙት ድብደባ የሰው ሂወት ያጠፉ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ወደየአስር ቤቱ በግፍ መጋዛቸው የሚታወስ ነው፡፡

በጅምላ ታፍሰው በአዲስ አበባ በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች እንዲበተኑ የተደረጉት ንፁሃን ሙስሊሞች እስር ቤቶቹ በመሙላታቸው በረንዳው ላይ ሳይቀር እንዲተኙ ሲደረጉ ነበር፡፡ይህም ሆኖ በዛሬው ዕለት ጁምአ በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ፖሊስ ጣቢያዎች ታስረው የሚገኙ ንፁሃን ሙስሊሞች በመታወቂያ ዋስ እየተፈቱ እንደሚገኙ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በዚህም መሰረት በቦሌ ክፍለ ከተማ አምቼ አካባቢ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ታሰረው የነበሩ ቁጥራቸው ከ390 በላይ የሆኑ ወንድምና እህቶች በመታወቂያ ዋስ መለቀቃቸው ተዘግቧል፡፤

በመቀጠልም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ጎተራ መንገድ ፔፕሲ ፊት ለፊት በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ ወደ 150 ከሚሆኑት ንፁሀን ሙስሊሞች መካከል 140 የሚሆኑት በመታወቂያ ዋስ መለቀቃቸው የተገለፀ ሲሆን የተቀሩት 10ሩ ዋስ የሚሆናቸው ባለመምጣቱ ሊለቀቁ አለመቻላቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፤

በተጨማሪም በኮልፌ ቀራኒዬ ክ/ከተማ ዘነበ ወርቅ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ከነበሩት ሙስሊሞች መካከል ከ 100 በላይ ንፁሃን ሙስሊሞች በመታወቂያ ዋስ መለቀቃቸው ተዘግቧል፡፤

በማሰር በመደብደብ በማሰቃየት የሙስሊሞችን አቋም ማስቀየር አይቻልም!!!!

ድል ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች!!!

No comments: