Wednesday, August 7, 2013

የለሊቱ አጫጭር መረጃዎች 2

ድምፃችን ይሰማ

የለሊቱ አጫጭር መረጃዎች 2

መንግስት በዒድ የሚኖረውን የሕዝብ
ማእበል ይገታልኛል ብሎ
ከተጠቀመባቸው ስልቶች አንዱ በወረዳ
ስራ አስፈጻሚዎችና የካድሬ አባላት
አማካኝነት በሁሉም የአዲስ አበባ
አካባቢዎች ቤት ለቤት በመዞር
ሙስሊሞች ለኢድ ሰላት እንዳይሄዱ
እንዲያሰፈራሩ እና እንዲያባብሉ ነበር፡፡
ይህ ስራ እስከዛሬ ምሽት ድረስ የቀጠለ
ሲሆን በተለይ በኮልፌ ቀራኒዮ፣ በጉለሌ፣
በቂርቆስ፣ በንፋስ ስልክ፣ በቦሌ እና
በአራዳ ክፍለ ከተሞች በስፋት ሲካሄድ
ነበር፡፡ ‹‹እባካችሁ ስታዲየም አትሂዱ፣
እዚህ ሰፈር መስጊድ ብትሰግዱ ይሻላል››
የሚሉት ተደጋግመው ከካድሬዎቹ አፍ
የሚወጡ ቃላት ናቸው፡፡ የሚገርመው
መንግስት መሰል ተግባር ባለፉት ሁለት
ዒዶች አሰርቷል፡፡ ውጤቱ ግን ዜሮ
ሆኖበት ነበር፤ ነገም ይህ ሕዝብ
ሚሊዮኖች ሆኖ በአዲስ አበባ
ስታዲየምና ዙሪያው በመፍሰስ
በካድሬዎች እና አጉል ፕሮፖጋንዳ
የማይታለል መሆኑን ያስመሰክራል፡፡
አላሁ አክበር!

No comments: