Monday, December 14, 2015

ናዝሬት/አዳማ ከቁጥትር ዉጭ ሆናለች የሚል ዜና ደርሶናል።

አዳማ ከፍትኛ የሆነ የህዝብ ተቃውም ተነስትዋል ፤የመንግሥት ደህንነቶች በኑፀሀን ህዝብ ላይ ጥይት በመተኮስ እየገደሉ ይገኛሉ።

በአዳማ ቱሉ በናዝሪት የተነሳው የህዝብ አመፀ ወደ ብጥብጥ ተቀይሮ በፌድራል ፖሊስ እና በልዪ ሀይል በተወሰደው እርምጃ ወደ 28 የሚጠጉ የናዝሪት ወጣቶች ተገደሉ፡
በሰላማዊ መንገድ ሲደርግ የነበረው አመፅ አድማ በታኝ ጭስ በመተኮስ ሰልፉን ለመበተን የታሰበ ቢሆንም አልበገርም ያለው ህዝብ በመንግስት ታጣቂወች ላይ እርምጃ ሲወስዱ ወደ ከፋ አመጸ ተቀይሮ፣ ከተማው ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ሆናለች።

የመንግስት ቢሮወች እና የአመመራሮች መኖሪያ፣ በእሳት እየተቃጠሉ ይገኛል፡ በተለያዩ የመንግስት ቢሮ በደረሰው ጥቃት፣ ከፍተኛ የሆኑ መረጃወችን የአዳማ ህዝብ በማቃጠል ላይ ይገኛሉ፡ እንዲሁም ተሽከርካሪወችን ጨምሮ የመንግስት ካድሬ እና ካቤኔ መኖሪያ ቤቶች በእሳት ጋይተውል።

Source: Millions of voices for freedom - UDJ 



No comments: