Sunday, December 13, 2015

በመላው አገሪቱ ውጥረቱ አደገኛ ደረጃ ላይ መድረሱ እየተነገረ ነው፡፡

በምስራቅ ጎጃም ደብረ ኤልያስ ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች ወጣቶችን እያፈሱ ነው፡፡ ወዴት እንደተወሰዱ እስካሁን ለማወቅ አልተቻለም፡፡

በአማራ አካባቢ እያየለ በመጣው ውጥረት አለመረጋጋት ውስጥ የገባው ወያኔ ወጣቱን እያፈሰ መሆኑን ከአካባቢው ባገኘነው መረጃ ለማዋቅ ተችሏል፡፡ በሌላ በኩል በደብረ ማርቆስ ህዝባዊ ቁጣ እያንዣበበ መሆኑ ከተማው በውጥረት ተከቦ ይገኛል፡፡ ትምህርት ቤቶች እየተጠበቁ ነው፡፡ በተመሳሳይ በባህር ዳር ውጥረቱ አይሏል፡፡ በአማራ ክልል ህዝቡ ከጫፍ እስከ ጫፍ በጎንደር ለሱዳን በሚሰጠው መሬትና በመላ አገሪቱ በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወጣቱን እያነቃቃው እንደሚገኝ ከነዋሪዎች በወቅታዊ ጉዳይ ያለውን ሁኔታ ጥቆማ አድርሰውናል፡፡ በዚህም ብአዴንወያኔ) በስጋት ተወጥሮ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል፡፡


በሌላ በኩል በአዲስ አበባ የስርዓቱ ካድሬዎች በወቅታዊ ጉዳይ በስጋት ላይ ይገኛሉ በስብሰባ ተጠምደው ተቃውሞ ከተነሳ እንዲጠነቀቁ እየተነገራቸው መሆኑ ከውስጥ መረጃ አድርሰውናል፡፡

No comments: