Friday, December 25, 2015

"ሞት እስር እና ስቃይ ሠላማዊ እና ሕጋዊ ትግል ፈጽሞ የሚያስቆም አይደለም' ትግሉ ይቀጥላል" ይላሉ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ይድነቃቸው ከበደ።


ሞት እስር እና ስቃይ ሠላማዊ እና ሕጋዊ ትግል ፈጽሞ የሚያስቆም አይደለም' ትግሉ ይቀጥላል" ይላሉ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ይድነቃቸው ከበደ።
አቶ ይነቃቸው የሚከተለውን ጦምረዋል
ትግሉ ይቀጥላል !
የአገዛዙ ሥርዓት የተለመደው አፈና እና እስር አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡በሙያው ሰለቸኝ ደከመኝ የማይለው ጋዜጠኛ Getachew Shiferaw ለእስር ተዳርጓል፡፡ ጌቾ የነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣና መጽሔት ዋና አዘጋጅ በመሆን ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት፤ ለሙያው ያለው ፍቅር እጅግ በጣም ድንቅ ነበር፡፡ሙያውን መሠረት አደርጎ ጠቃሚ መረጃዎች ለህዝብ እንዲደርስ ያደርግ የነበረው ጥረት እና ፍላጎቱ ጋዜጠኝነት በድም-ሥሩ የገባ ምርጥ ሰው !
ይሁን እንጂ ብዕርን እንደ-ጦር የሚፈራው የህውሓት/ኢህአዴግ አምባገነን መንግሰት ጋዜጠኛ#‎ጌታቸው_ሽፈራው‬ ከቤቱ አፍነው ወስደዉታል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ የጀርባ አጥንት ከሆኑት መካከል ወጣት #‎ቴዎድሮስ_አስፋው‬ እና #‎ዳንኤል_ተስፋዬም‬ በዛሬው ዕለት መታሰራቸው ለማወቅ ተችሎአል፡፡እነዚህ ሁለት ወጣቶች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መታሰራቸው የሚታወስ ነው፡፡ሞት፣እስር እና ስቃይ ሠላማዊ እና ሕጋዊ ትግል ፈጽሞ የሚያስቆም አይደለም!!!


No comments: