Monday, December 14, 2015

የግፈኞችን ትእዛዝ አልቀበልም ብሎ ዩኒፎርሙን አቃጠለ - የሚሊዮኖች ድምጽ


መከላከያ ዉስጥ መከፋፈል እንደተፈጠረ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ሙሉ ለሙሉ ፈርሷል ወይንም እንዳይንቀሳቀስ ተደርጓል ማለት ይቻላል። የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስተር፣ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የት እንዳሉ አይታወቅም።

በዘጠና ሰባት በአዲስ አበባ እንደተደረገው በኦሮሚያ ልዩ እዝ የተቋቋመ ሲሆን፣ ይህ እዝ ነው በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ግድያዎች እንዲፈጸሙ እያዘዘ ያለው። እዙ ለስሙ በጠ/ሚኒስትሩ ይመራል ቢባልም፣ በጀነራል ሶሞራና ጌታቸው አሰፋ (ሕወሃቶች) የሚመራ እዝ ነው።

እነ ሶሞራ በባሌና በምስራቅ ሃረርጌ፣ የኦሮሞ ፖሊሶችንና መከላከያዎችን ስላላመኑ፣ በሶማሌና በኦሮሞ መካከል ጠብ ለመፍጠር የሶማሌ ሚሊሻዎችን እያሰማሩ ሲሆን፣ በሸዋ ደግሞ ታማኝ የብአዴን ካድሬዎችን በማሰለፍ በአማራዉና በኦሮሞው መካከል የዘር ግጭት ለመቀስቀስ እየሰሩ ነው።

ሕወሃቶች በስልጣን ለመቆየት ያላቸው ብቸኛ መነግድ በተለይም አማራዉን እና ኦሮሞዉን ማጋጨት በመሆኑ፣ ያንን ለማድረግ ብዙ ገንዘን አውጥተው ቀዉስ ለመፍጠር ስለሚሞክሩ፣ በዚህ ረገድ ሕዝቡ ትልቅ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰቢያዎች እየተሰጡ ነው።
ከዚህ በታች የምትመለከቱት የወያኔ ወታደር የነበረ ኦሮሞ፣ ግፈኞችን አልታዘዝም ብሎ ዩኒፎርሙን አወልቆ ሲያቃጥል ነው።


No comments: