Friday, December 18, 2015

"ውጥረቱ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል!?

ህውሓት ሊያበቃለት ነው፡፡በአዲስ አበባ እያንጃበበ ያለውታቃውሞ ሊፈነዳ የደረሰ መሆኑ ከየአካባቢው ከሚመጡመረጃዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአገሪቱ የሚታየው የህዝብተቃውሞ እንቅስቃሴ እየተንከባለለ ሸገር ሊገባ ነው፡፡ ወጣት
አዛውንቱ በወቅታዊ የአገሪቱ ሁኔታ እየተነጋገረ ነው፡፡ ወጣቱበቃኝ ብሎ ሊነሳ ነው፡፡ ህውሓት ተጨንቋል፡፡በአዲስ አበባወጣቱን በአበል ለመሰብሰብ በየቀበሌው ካድሬው ቢራወጥም
የሚሳካ አልሆነም፡፡በኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ አመጽ የአዲስአበባ ወጣትን እያነቃቃው መሆኑ በዚህ ቀን ሳይባል ድንገትየሚፈነዳ የህዝብ ብሶት እንዳለ በየአካባቢው ያሉ ወጣቶችን
በመነጋገር ሁኔታውን በቅርብ ከሚከታተሉ ወገኖች ስጋታቸውንእየገለጹ ነው፡፡ሁሉ ነገር ጨልሟል የታክሲዎች እንቅስቃሴበውጥረቱ ምክንያት ቀዝቅዟል፡፡አብዛኞዎቹ ሳይታሰብየሚገነፍል ቁጣ ይመጣል በሚል አቁመዋል፡፡አዲስ አበባየሚኖሩ የባለስልጣን መኖሪያ ቤት ከዚህ ቀደም ባልነበረ
የወታደር ጋጋታ እየተጠበቀ ነው፡፡ የመረጃው ምንጮች እንዳሉትቦሌ 03-05 አካባቢ እንዲሁ(መካኒሳ አቦ ማዞሪያና ብስራተ
ገብርኤል መንደር ብዛት ያለው ሰራዊት ፈሷል በሌላ በኩልማረሚያ ቤቶችና ድርጅቶች በሚበዙበት አካባቢ በከባድ መሳሪያጭምር እየተጠበቀ መሆኑ ስጋቱ ምን እንደሚመስል ያሳያልሲሉ የሚናገሩ ብዙ ናቸው፡፡በአዲስ አበባ እየመጣ ያለውተቃውሞ ሳይታወቅ ሊፈነዳ የሚችል በመሆኑ ለታማኝካድሬዎች እራሳቸውን ህዝብ ከሚበዛበት እንዲርቁና ነቅተውእንዲጠብቁ ተነግሯቸዋል፡፡ከአለም ባንክ ወደ ጀሞ ጥቁር
በመልበስ በድምጽ አልባ ተቃውሞ በመንገድ ሲሄዱ የነበሩወጣቶች እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል፡፡ መረጃውን ለማጠናከርእየፈለግን ነው፡፡
በሌላ በኩል በደብረ ማርቆስ ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ እየተነገረነው፡፡ በደብረ ማርቆስ ቀበሌ03 ልዩ ስሙ አምረት በሚባልሰፈር በቀበሌ ቤት የሚኖሩ ሰዎችን በማፈናቀል ቦታውን በሊዝ
እየተሸጠ ነዋሪዎችን ከከተማው ዳር እያሶጡ መሆኑ ከነዋሪዎችበተገኘ መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአሁን ሰዓት በደብረ ማርቆስ
እንዲሁም በባህር ዳር በአማራ ህዝብ በጎንደር የሚደርሰውየህውሓት የማጋጨት ሴራ ለሱዳን በሚሰጠው መሬትበአማራው ላይ በሚደርሰው ጭቆና ህውሓትብአዴን)ህዝቡ በቃሊል ከጫፍ መድረሱ ከሚመጡት የህዝብ ድምጽ እየተሰማ
ነው፡፡ በመላው ኦሮሚያ እየተቀጣጠለ የመጣው ህዝባዊንቅናቄ)በአማራው ሊደገም እንደሚችል ምልክቶች እንዳሉሁኔታውን በቅርብ ከሚያውቁ ሰዎች ለመስማት ተችሏል፡፡
የጎንደር ህዝብ ከስርዓቱ ጋር እየተናነቀ መሆኑ ተቃውሞ ወደጎጃም ሸዋ ወሎ እየተዛመተ ከሄደ እንዲሁ በመሀል አገርከተጀመረ በቀናት ውስጥ ህውሓት)ሊያበቃለት እንደሚችል
ብዙዎች ይናገራሉ፡፡


No comments: