Wednesday, December 16, 2015

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በምስክርነት እንደማያቀርብ አሳወቀ



የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሰውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በምስክርነት እንደማያቀርበው ለልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ ማረሚያ ቤቱ ታህሳስ 4/2008 . ለልደታ ፍርድ ቤት በላከው ደብዳቤ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ‹‹18 አመት ፅኑ እስራት የተፈረደበት በመሆኑና ከአሁን ቀደም ምስክር ሆኖ ከማረሚያ ቤቱ ወጥቶ መስክሮ ስለማያውቅ ለመስክርነት ለማቅረብ እንቸገራለን›› ብሏል፡፡
እስክንድር ነጋ ለእነ ዘላለም ወርቃገኘው በመከላከያ ምስክርነት ከተቆጠረ በኋላ ከህዳር 13 /2008 . ጀምሮ ለአራት ቀጠሮዎች በምስክርነት ሳይቀር የቀረ ሲሆን ዛሬ ታህሳስ 6/2008 . ማረሚያ ቤቱ በላከው ደብዳቤ መሰረት ሳይቀርብ ቀርቷል፡፡ ከአንድ አመት በፊት 6 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ተኩል 30 ደቂቃ ሲጠየቅ የነበረው እስክንድር ነጋ በአሁኑ ወቅት እንዳይጠየቅ ተከልክሏል፡፡ በተጨማሪም ማረሚያ ቤቱ በተደጋጋሚ እስክንድር ነጋ የታሰረበትን ክፍል በመፈተሽ መፅሃፍ ቅዱስን ሳይቀር መነጠቁም ይታወሳል፡፡


Source: ነገረ ኢትዮጵያ

No comments: