Wednesday, December 23, 2015

በነ ኦነግና ግንቦት ሰባት አታሳቡ ይላል ሪፖርተር ጋዜጣ - የሚሊዮኖች ድምጽ



ገዢው ፓርቲ ሕወሃት/ኢሕአዴግ በኦሮሚያና በጎንደር ለተከሰተው ቀዉስ ጣቶቹን በዉጭ ያሉ አመጽ ቀስቃሽ ኃይሎች በሚላቸው ላይ ማድረጉ ይታወሳል። አቶ ጌታቸው ረዳ የመንግስት ቃል አቀባይም አፋቸዉን ሞልተው ተቃዉሞ ያሰሙትን በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንንጋኔኖች በዉጭ ያሉጋኔኖችንየሚያንቀሳቀሱ ያሉዋቸዉን ደግሞጠንቁዋዮችየሚል ከአንድ ትልቅ አገር የመንግስት ቃላቀባይ በጭራሽ የማይጠበቅ ርካሽ ንግግር መናገራቸው ይታወሳል።
አገር ዉስጥ የሚታተመው ሪፖርት ጋዜጣ ግን አይስማም። የተፈጠረው ችግር የዉጭ ኃይሎች የሚባሉ ያመጡት ሳይሆን የስርዓቱ ጸረ-ዴሞክራሲያዊ አሰራር የፈጠረው እንደሆነ ሪፖርተር በርእስ አንቀጹ ተንትኑዋል። በሌለ አባባል ሪፖርት ከአገዛዙበነ ኦነግና ግንቦት ሰባት በመሳሰሉት አታሳቡ። ችግሩ ያለው እናንተ ጋር ነውማለቱ ነው።
ድምጻቸው እንደታፈነባቸው የሚሰማቸው ወገኖች፣ ሕገ መንግስቱን ያረጋገጠላቸው መብትና ነጻነት ባለመከበሩ ምክንያት ሁከት ማንሳታቸው ሳይነገር፣ ከበስተጀርባ ስላሉ ኃይሎች በብዛት ሲነገር ይሰማል። አንድ ዜጋ መሰረታዊ መብቶቹ ከተከበረለትና በአገሩ በነጻነት እየኖረ መሆኑን ማረጋገጥ ከቻለ፣ ከድህነት ሊያወጣው የሚችልን ልማት ሊቃወም አይችልም፡፡ሌላ ፍላጎት ላላቸውም መሳሪያ አይሆንምያለው ሪፖርተርመንግስት ይህንን በፍጥነት በማጤን ሕግ መንግስቱን ማስከበር አለበት። ሕግ መንግስቱ ሳይከበር ቀርቶ ድንገተኛ አመጽ እየተከሰተ የዜጎችን ሕይወት የሚቀጥፍበት ምንም ዓይነት ሰበብ ሊኖር አይገባም። መንግስትም በግባትዊነት የሚፈነዱ ብጥብጦች ከሕግ የበላይነት መጥፋት ጋር የታያያዙ መሆናቸው የግድ ማመን አለበት። ከበስተጀርባ አሉ የሚባሉ ኃይሎች አመጹን የመምራት እድል የሚያገኙት ዜጎች መብታቸው ሳይከበርላቸው ሲቀር መሆኑ መታወቅ አለበት። የሕዝብን መሰረታዊ መብቶች የሚጋፉ ተግባራት ይወገዱሲል አገዛዙ የችግሩ መንስኤ ዋና የሆነው፣ አምባገነናዊ አሰራር እንዲወገድ ጠይቁዋል።
ሕወሃት/ኢሕአዴ ለዲሞክራሲ ቆሚያለሁ እያለ የሚመጻደቅ ደርጅት ነው። የደርጅቱ መሪ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ስለ ዲሞክራሲ ብዙ ጊዜ ሲናገሩዴሞክራሲ የሕልዉና ጉዳይ ነውይላሉ።
ሪፖርት ግን አገዛዙ ለዲሞርካሲ ያለውን ቁርጠኝነት ትልቅ ጥያቄ ምልክት ዉስጥ ውስጥ ያስገባዋል ።በሌላ አባባል፣ ዲሞክራሲ፣ ዲሞርካሲ እያላችሁ፣ በከንቱ ህዝቡን ባትዋሹና ራሳችሁን ባታስገመቱ ይሻላል ነው ሪፖርት እያለ ያለው።
የዜጎች ድምጽ የሚሰማባቸውን መድረኮች አለመክፈቱ ትልቅ ፈተና ነው። የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የተለዩ ድምጾች ካልተሰማባቸው፣ አመለካከትን በነጻነት የሚገልጹባቸው መድረኮች ከሌሉ፣ ሰላማዊ ሰልፎችና ሕዝባዊ ዉይይቶች ካልተከናወኑ፣ የዜጎችን ሐሳቦች የሚያስተጋቡ የሲቪል ማህበራት ከጠፉ፣ በፖለቲካ ምህዳሩ መጣበብ ምክንያት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከተልፈሰፈሱና መሰረታዊ መብቶች ካልተከበሩ ዴሞክራሲ ማለት ምን ማለት ነው ?” ሲል ሪፖርት በመጠየቅ ነው፣ የዛሪይቱ የሕወሃት/ኢሕአዴግ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ የሰፈነባት ሳይሆን ዲሞክራሲ የራቃት እንደሆነ ለማሳየት የሞከረው።
ገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ብዙ ጊዜ ሕግ መከበር እንዳለበት በአደባባይ ሲሰብኩ ይሰማሉ።ሕገ መንግስታችንይላሉ። ሆኖም ብዙ ጊዜ ሕዝቡ በሚያሰማቸው ተቃዉሞዎችሕገ መንግስቱ ወረቀት ብቻእንደሚባለው፣ ሪፖርተር ጋዜጣም በመስማማት፣ሕግ መንግስቱ ካልተከበረ በጽሁፍ ሰፍሮ መቀመጡ ምን ይጠቅማል ? “ ሲል ተግባር በሌለበት ሁኔታ ያለው ሕግ መንግስት ጥርስ የሌለው ወረቀት ብቻ እንደሆነ ነው ለመገልጽ ሞክሩዋል።
የሪፖርተርን ሙሉ ረስ አንቀጽ ለማንበብ ከታች ያለው ይጫኑ


Source: ethiopianreporter 


No comments: