Tuesday, December 15, 2015

ደግሜ አስጠነቅቃለሁ - ግርማ ካሳ

ላለፉት በርካታ አመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እየከረረ ነው፤ ብሄራዊ እርቅ ያስፈልጋል እያልን ስንጎተጉትና ስንጽፍ ነበር። ህዝብ ይሄንን መንግስት በጣም እንደሚጠላ፤ ሕዝብ ጨዋ ስለሆነ ታግሶ እንጂ የመረረው እለታ ጉድ እንደሚፈላ ስንናገርና ስናስጠነቅቅ ነበር። ሰዎቹ አልሰሙንም። ጭራሽ 100% አሸነፍን ብለው ለሕዝብ ያላቸውን ንቀት በገሃድ አሳዩ።
ከአንድ ሶስት ወራት በፊት በዲቪ የመጣ አንድ የመንግስት ሰራተኛነገሮች በጣም ታምቀዋል። ሰው በጣም ነው የጠላቸው። There is a gathering storm” ነበር ያለኝ። እንደውም ይሄ ሰው አሁን የስርዓቱ ተጠቃሚ የሆኑቱን ጥቂቶቹንዜጎችብሎ ነበር የሚጠራቸው። ለምን ብዬ ስጠየቅእነርሱ እንጂ እኛ እኮ ዜጎች አይደለንም”” ነበር ያለኝ። ያን ያህል ነበር ጥላቻዉን የገለጸልኝ።
ይኸው እንዳስጠነቀቅነው እየሆነ ነው። ሕዝቡ ተቃውሞዉን እያሰማ ነው። ወያኔዎች ነገሩ ከቁጥጥር ዉጭ ሆኖባቸዋል። ከአንድ ሳምንት በፊት አምቦን አረጋግተናል ብለው ነበር። ብዙ ሰው ገድለዉና አስረው። ሆኖምስንገድለው፣ ስንድበድበው አፉን ይዘጋልያሉት ሕዝብ እንደውም የበለጠ አምርሮ ወጣ።
አምቦ ብቻ አይደለም፤ በአምቦና በአዲስ መካከል ያለችው ቡራዮም የጦርነት አውድማ ሆናለች። የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሱቆች በሙሉ ተዘግትተዋል። ከቡራዪ አዲስ አበባ መንገድ የለም።እንግዲህ ቡራዮ ማለት ትንሽ ሄድ ካልን አስኮ፣ ከዚያም ጉለሌ ነው የምንደርሰው።
አዲስ አበባ አፋንጫ ላይ ያሉትን አገዛዙ ማረጋጋት ካልቻለ፣ እንደ ዶዶላ፣ ባኮ፣ ነጆ፣ ቆቦ..ያሉትን እንዴት ነው የሚያረጋጋው ??
በጉልበት፣ በኃይል ይሄን አይነት እኔ በእድሜዬ አይቼ የማላወቀዉን ተቃዉሞ ማስቆም የሚቻል አይመስለኝም።
ለጊዜው አሁን እያደረጉት እንዳለው ብዙዎችን በመግደልና በማሰር ለጊዜው መረጋጋት ቢያመጡም፣ በከፋ ሁኔታ እንደገና አመጹ መቀስቀሱ አይቀርም። አሁን ህዝቡ በሰላም ነው እጆቹ እየዘረጋ ድምጹን የሚያሰማው። ግን እየከፋ ከሄደ፣ ጣሊያን ፋሺስትን ባለው መሳሪያ ሁሉ እንደመከተ መሳሪያዉን እና ጎራዴዉን መወልወል መጀመሩ አይቀሬ ነው። ያን ጊዜ የሰላም ሳይሆን የአመጽ እንቅስቅሴ ነው የሚሆነው። ያን ጊዜ በአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን በሌላኛውም ወገን እልቂት ይጀመራል። አገሪቷ ወደ ሶሪያ አይነት የርስ በርስ ጦርነት ዉስጥ ትዘፈቃለች። በዙህ ሂድት ደግሞ 200% የሚከስሩት ሕወሃቶችና ደጋፊዎቻቸው ነው። ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው። ማን ምን እንደሆነ በሚገባ ይታወቃል።
በመሆኑም በአስቸኳይ የወያኔ ታጣቂዎች ተኩስ አቁመው፣ ተቃዉሞ ከሚሰማባቸው ቦታዎች ለቀው እንዲወጡ እንጠይቃለን። እነርሱ ባሁኑ ጊዜ ለሕዝቡ አለርጂክ ናቸው። የነርሱ ብቅ ማለት ህዝቡን የበለጠ ያስቆጣል።
አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአሁኑ ጊዜ የት እንዳሉ አይታወቅም። አሻንጉሊት መሆናቸው ሰሞኑን በገሃድ ታይቷል። እንደ አንድ መሪ በዚህ ወቅት በቴሌቭዝን ቀርበው ህዝቡን ባይሰማቸውም እንኳን፣ ለማረጋጋት መሞከር ነበረባቸው። አላደረገትም።
ሆኖም ግን፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እንደመሆናቸው፣ ቢያንስ በዚህ ወቅት ድፍረት አግኝተው፣ ቆራጥ ዉሳኔ ያሳለፉ ዘንድ እንጠይቃለን። ስልጣኑ በሕግ አላቸው። እርግጠኛ ነኝ ፓርላማውንም ቢሰበስቡ፣ 5% ብቻ ሕወሃቶች ያሉበት ፓርላማ ከጎናቸው ይሰለፋል። እነ ሶምራ የነሱስ፣ እነ ጌታቸው አሰፋ፣ ኢትዮጵያን አኬልዳም (የደም መሬት) ሲያደረጉ ዝም መባል የለባቸውም። አቶ ኃይለማሮያም ሊያስቆሟቸው ይገባል። በዚህ ወቅት አቶ ኃይለማሪያም ዝምታን ከመረጡ ግን ለሚፈሰው ደም ሁሉ እርሳቸውም ተጠያቂ ነው የሚሆኑት።
አጋዚ ሕዝብ ከሚኖርበት ከተማ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ፣ ለተፈጠሩት ችግሮች የፖለቲካ መፍትሄ መፈለግ አለበት። ሕዝብ አገዛዙን ተፍቶታል። ኢሕአዴግ የመግዛት ሞራል ብቅት የለዉም። አገዛዘን እንዳለ ስልጣን ላይ የሚያቆይ ኮስሜትክ ለዉጥን ህዝቡ አይቀበልም። በመሆኑም አቶ ኃይለማሪይም የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም በማድረግ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ቢያደረጉ ጥሩ ነው።
አሁን 11 ኛው ሰዓት፣ አምሳ ዘጠነኛው ደቂቃ ላይ ናቸው። በኦሮሚያን በጎንደር የተነሳው ተቃዉሞ የአዲስ አበባ ህዝብ ወይንም የጎጃም ወሎ የመሳሰሉት ከተቀላቀሉት፣ ሁሉም ነበር አበቃ ማለት ነው። ህዝቡ ያኔ በሕይወታቸው ነው የሚዉጣቸው። ለራቸው የሚበጅ ነገር ማድረግ ካለባቸው ማድረግ ያለባቸው አሁን ነው።


No comments: