Monday, December 21, 2015

የሕወሃት ደህንነት የኦህደድ አመራሮችን ለማሰር አቅዱዋል

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - ዛሬ ከከሰአት በኋላ ጀምሮ በአዲስ አበባ የደህንነት ቢሮ ውስጥ የሕወሓት ማፊያዎች ተሰብስበዋል::ስብሰባው ያተኮረው ባለፉት ሳምንታቶች ተከስቶ ስለነበረው በሕዝብ ተመርቶ በሕዝብ ስለተካሄደው እና ያልተሳተፉ ድርጅቶች አቀናጁት የተባለው ሕዝባዊ ንቅናቄ ዙሪያ እና አንዲሁም ይህንን ንቅናቄ በተመለከተ የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ሹሞች ፍርሃት ብሎም የአስተዳደር ባለስልጣናት ሽሽት እና አመጹን ከመቆጣጠር ይልቅ አባብሰዋል ስለተባሉ የኦሕዴድ/ኢሕኣዴግ ሰዎች ሁኔታ እና መወሰድ ስላለበት እርምጃ በመወያየት ላይ ሲሆን ቀጥሎ ስላለው አፈና እና አመጽ ሳይነሳ መደምሰስ የሚቻልበትን ጉዳይ በተመለከተ በሪፖርቶች ዙሪያ እስከ እኩለ ለሊት ይነጋገራል ተብሎ ይጠበቃል::
ሕዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ የሕዝብን የመብት ጥያቄ እንዴት ልደፍጥጥ የሚለው የሕወሓት መራሹ አገዛዝ በኦሮሚያ ክልል በተደረጉ ይሁኑ በጎንደር እየተደረጉ ባሉ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ዙሪያ በስብሰባም ይሁን በውሳኔ ሰጭነት የክልሉን ተወላጅ ባለስልጣናት ያላሳተፈ መሆኑ ታውቋል ሲሉ የደህንነት ቢሮው ምንጮች ለምንሊክሳልሳዊ ተናግረዋል:: ይህ የደህንነት ቢሮ ስብሰባ በቀጥታ እስኔው ወርዶ የሕወሓት አሽከር ድርጅቶች እንዲያስፈጽሙት እየተደረገ ሲሆን የዛሬውን ስብሰባ በሕወሓቶች በትግሪኛ ቋንቋ እየተካሄደ ይገኛል:; የዛሬውም ውሳኔ በቀጥታ እንዲያስፈጽሙ የሚደረጉ የአሽከር ድርጅት አባላት ሲሆኑ በበላይነት የሕወሓት ሰዎች አፈጻጸሙን ይከታተላሉ::ይህ የተለመደ አሰራር እስከመቼ እንደሚቀጥል ባይታወቅም ተቃውሞውን ተከትሎ በኦሕዴድ እና ብኣዴን አባላት ላይ ጠንካራ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ እንደሚደረግ ከስብሰባው በኋላ ይጠበቃል::
በሕዝባዊ ንቅናቄው የሕወሓት መንግስት እንደተነቃነቀ የደህንነት ቢሮው ከቀኑ 10 ሰአት ላይ ለሻት ከመውጣታቸው በፊት ባቀረበው ሪፖርት አሰታውቋል::ከፍተኛ ባለስልጣናት ሃገር ጥለው ለመሸሽ አኮብክበው ነበር ያለው የቢሮው ሪፖርት በመካከላችን መተማመን ስላሌለ አዲስ መዋቅር መዘርጋት ይኖርብናል ሲል አሳስቧል::በመካከላችን መተማመን የለም ያለው በሕወሓት ባለስልጣኖች እና በሌሎች ድርጅት ባለስልጣኖች መካከል መሆኑን ጠቁሟል::
በተለይ የኦህዴድ ሹሞሽ ከነአጋሮቻቸው ተለቅመው ሊታሰሩ እንደሚገባ ሃሳብ ቀርቧል::ብተጨማሪም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ሰርጎ ገቦችን በማስገባት በተለያየ መንገድ ውጣቱን ማኮላሸት እና አልኮላሽ ያለውን በማፈስ ከክልሉ ውጩ በሚገኙ ማጎሪያ ካምፖች ለማስር ሲታቀድ ሰሞኑን ተሳትፎ የነበራቸው ወጣቶችን የማፈን እቅዱ በሂደት እንዲከናወን በሪፖርቱ ላይ ሃሳብ ቀርቧል::ብቻችንን ቀርተናል ያለው ሪፖርት በቀጣይነት አስፈላጊ ሃይል እና ምስጢራዊ አፈናና ግድያ እንደሚጠቀም አትቷል::ይህንን መረጃ የሰጡ የመዋቅሩ አካላት ሕብረተሰቡ በጋራ ራሱን እና አከባቢውን በመጠበቅ ሰርጎ ገብ ጸጉረ ልውጦችን በመከታተል ከአከባቢው እንዲያሶግድ እና እርስ በእርሱ እንዲጠባበቅ የኦሕዴድ እና የብኣዴን ካድሬዎች የሕወሓት ካድሬዎችን ሳያምኑ በጥንቃቄ ሁኔታዎችን በመከታተል ራሳቸውን እንዲያድኑ መክረዋል::


No comments: