Thursday, December 31, 2015

‹‹በሰላማዊ ትግል ላይ ትላንትም እምነት ነበረኝ፤ ዛሬም እምነት አለኝ፤ ነገም እምነት ይኞረኛል!›› እስክንድር ነጋ



በኢዮኤል ፍሰሐ
በሽብርተኛነት ተፈርጆ በአገዛዙ 18 ዓመት እስራት የተበየነበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ትላንት ታህሳስ 20 ቀን 2008 . በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19 ወንጀል ችሎት ቀርቦ ነበር፡፡ እስክንድር በችሎት የተገኘው በሽብርተኝነት የተከሰሰው ዘላለም ወርቅአገኘሁ ለመከላከያ ምስክርነት ስለጠራው ነበር፡፡ እስክንድር በችሎት ከሕሊና እስረኛው ሐብታሙ አያሌው ጋር አውግቶ ነበር፡፡ ሐብታሙ እንደገለፀልኝ ከሆነ ከእስክንድር ጋር በነበራቸው ወግ ስለ ቀድሞ አንድነት ፓርቲና ስለሰላማዊ ትግል ለጥቂት ደቂቃዎች ተነጋግረዋል፡፡ እስከንድር አሁንም በሰላማዊ ትግሉ ላይ ፅኑ እምነት እንዳለው ገልጿል፡፡
‹‹በሰላማዊ ትግል ላይ ትላንትም እምነት ነበረኝ፤ ዛሬም እምነት አለኝ፤ ነገም እምነት ይኞረኛል!›› ሲል መልዕከቱን አስተላልፏል፡፡ ይህ መልዕክቴ ለሁሉም ይድረስ ማለቱን ሐብታሙ አያሌው ዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2008 . ቂሊንጦ ተገኝቼ በጠየኩት ሰአት ነግሮኛል፡፡ እስክንድር ላለፈው አንድ ዓመት በማንም እንዳይጠየቅ ማረሚያ ቤትኃላፊዎች ዘንድ ተከልክሎ ይገኛል፡፡


No comments: