Tuesday, December 15, 2015

በለው በለው ወያኔ እሚይዘው እሚጨብጠው እየጠፋው ነው

ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሀይል ማፍረስ እንደማይቻል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ገለፀ


የህዝብ ጥያቄን ለጠባብ የፖለቲካ ፍጆታ በማዋል ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሀይል ማፍረስ እንደማይቻል የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገለፀ፡፡
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የክልሉን መንግስት አቋምን በሚተነትነው ፅሁፍ ላይ እንደተገለፀው በክልላችን የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ማረሚያ ቤቶችን በመስበር፤ የህግ ታራሚዎችን የመልቀቅ፣ የፖሊስ ጽህፈት ቤቶችን፣ የልማት ድርጅቶችን፤ የአርሶ አደር ምርቶችን፤ የግል መኖሪያ ቤቶችን በማቃጠልና በማውደም በጦር መሳሪያ በመታገዝ የጥፋት ተግባራቸውን በመፈፀም ላይ ያሉ ፀረ ሰላም ሃይሎች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል፡፡
እነዚህ ፀረ ሰላም ሃይሎች አብሮ የመኖር፤ መቻቻልና ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ተምሳሌት የሆነውን የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ብሄር ብሄረሰብ ወንድሞቹ ጋር የጎሪጥ እንዲተያይ፤ እንዲሁም በእምነቶች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ ከድርጊታቸው ጎን የቆመን ሀይል ሁሉ አሰልፈው ወደ ህገ ወጥ ተግባር ተሸጋግረዋል፡፡
በመሆኑም መንግስት የእነዚህን የጥፋት ሀይሎች ያልተገባ ዴሞክራሲያዊ ስርአቱን የመናድ ተግባር ለማስቆምና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በህገመንግስቱ የተጣለበትን ግዴታ መሰረት በማድረግ በድርጊቱ ዋና ተዋናዮች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል፡፡
ግብረ ሃይሉ በወቅታዊው የክልሉ ጸጥታ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረውን ሁከት በቁጥጥር ስር ለማዋል ህብረተሰቡ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር እያደረገ ያለው ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ጸረ ሽብር ግብረ ሃይል አሳሰበ፡፡
ጨቋኙና ጸረ-ዲሞክራሲውያዊው ደርግ ስርዓት በህዝቦች ትግል ከተገረሰሰ በኋላ የሀገራችን ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ድሎች ባለቤት መሆናቸው ይታወቃል፡፡
የሀገራችን ህዝቦች በተለይም በ1987 ዓ.ም ባጸደቁት ህገ-መንግስት ሠላማቸው ተረጋግጦ፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብታቸው ተከብሮ፣ በማንነታቸውና በቋንቋቸው ኮርተው ፊታቸውን ወደ ልማትና ዕድገት በማተኮር የብልጽግና ጎዳና ላይ እየተረማመዱ ይገኛሉ፡፡
ለዚህ ማረጋገጫው ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የዕድገት ስኬቶች ተጠቃሽ ሲሆን በዚህም ህዝባችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ ይገኛል፡፡
ካለፈው ህዳር ወር 2008 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ በአንዳንድ የከፍተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ውስን ቁጥር ያላቸው የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች የሆኑ ተማሪዎች ከፊት ለፊት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም ከበስተጀርባ ከውጭ ዘወትር ለሀገራችን ህዝቦች ሠላምና ዕድገት እንቅፋት መሆናቸውን በገሃድ ካስመሰከሩ የሽብር ቡድኖች የሚሰጣቸውን ተልዕኮ አንግበው ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ጋር ቀጥተኛ ትስስር በመፍጠር ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን አስተጓጉለዋል፡፡ እንዲሁም ከትምህርት መዋቅሩ ውጭ ሚገኘውና ከፍ ሲል ከተገለጸው የሽብር ቡድን ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት በመፍጠር የነውጡና ረብሻው አድማስ ወደ ከተሞችና ወደተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲስፋፋ በማድረግ በርካታ የመንግስት፣ የግል ባለሃብቱና የደሃው አርሶ አደር ንብረትና ሃብት እንዲወድም አድርጓል፡፡ የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት ለመጠበቅ በተሠማራው የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አባላትና ጀግናው መከላከያ ሃይላችን አባላት ላይ የሞትና የአካል መጉደል አደጋ አድርሷል፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ግብረ-ሃይል በአገራችን የብሄር ብሄረሰቦች ቃል-ኪዳን የፀደቀውንና እየተገነባ የመጣውን ህገ-መንግስታዊ ስርዓትንና የህዝቡን ሰላማዊ የመኖርና የመንቀሳቀስ ህገ-መንግስታዊ መብቱንና ነፃነቱን ለማረጋገጥ፤ አስተማማኝ ለማድረግ በሽብርና በአመፅ ሃይሉ ላይ የሚያደርገውን ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ የፀረ-ሽብር ግብረ ሃይሉ ይህንን እርምጃ በተከታታይነት ሲወስድ የአገራችን ብሄር ብሄረሰቦች ሁሌም እንደሚያደርገው አካባቢያቸውን በመጠበቅና ከፀጥታ ሃይሎች ጎን በመቆም የበኩላቸውን እንዲወጡ እያስገነዘበ በተለይም ችግር ጎልቶ በሚታይባቸው አካባቢዎች የሚኖረው ህዝባችን እስከአሁን የሽብርና የአመጽ ሀይሎችን እኩይ ተግባር ከማክሸፍና አካካቢያቸውን ከመጠበቅ ባሻገር ከጸጥታ ሀይሎች ጎን ለጎን በመቆም እየተፋለሙ የህይወት መስዋዕትነት ጭምር እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡ ለዚህም ግበረ ሀይሉ ለህዝባችን ያለውን አድናቆትና ክብር በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ ይወዳል፡፡
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሚገኙ የከፍተኛና ሁለተኛ ደረጃ የሚማሩ ተማሪዎች በርካቶቹ ሂደቱን በመቃወምና በመኮነን ትምህታቸውን እየቀጠሉ የሚገኙ ከመሆኑም በላይ መደበኛ ትምህርቱን ወደጎን በመተው የሽብርና የአመፅ ሃይሉ ሰለባ የሆኑ ተማሪዎችን አጋልጦ በመስጠትና የመማር ማተማር ሂደቱን ሰላማዊ ለማድረግ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛሉ፡፡
በገጠር ሆነ በከተማ የሚኖረው ህዝባችን አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት በትህምህርት ተቋማትም ሆነ ከትምህርት ተቋማት ውጭ የሚገኙትን ልጆቹንና መላ ቤተሰቡን የሰው ህይወት እንዳይጠፋና ንብረት እንዳይወድም፤ ዘረፋ እንዳይስፋፋ፤ የሽብር የአመጽ አቀጣጣዩች ሰለባ እንዳይሆን በማድረግ የበኩሉን ሚና እንዲጫውት ግብረ ሃይሉ ያሳስባል፡፡
Source: ebc.et


No comments: