Tuesday, December 22, 2015

በአዲስ አበባ ሰማያዊ ከመድረክ በጋራ የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ እውቅና አላገኘም መባሉን ፋና ዘግቧል፡፡

መድረክ ታህሳስ 17 ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ያስገባው የእውቅና ጥያቄ ተቀባይነት አለማግኘቱ ተገለፀ

ኢህአዴግ ጥቂት ፀረ ሰላም በሚላቸው ላይ ቀድሞ ተቃውሞ ለማድረግ 15 የተጠረነፉ አረጋዊያን አባሎቹና የኮብልስቶን ምሩቅ እንዲሁም የደረቅ ቆሻሻ ጽዳት ሰራተኞች ወረቀት እየተበተነ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ኢህአዴግ በህዝባዊ ሰልፍ ጥያቄ ቀደም ሲል ጀምሮ የሚያንጸባርቀው ምን እንደሆነ ከባህሪው መረዳት እንደሚቻል የሁለቱም ፓርቲ ፖለቲከኞች አይጠፋቸውም፡፡
ሳልቀደም ልቅደም የወቅቱ አጀንዳ ለፕሮፓጋንዳ ለማዋል አንዱ ለመሆኑ ወያኔ በካድሬው በኩል ውስጥ ለውስጥ እየተራወጠ ነው፡፡ በሌላ በኩል ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ህገ መንግስታዊ መብትን እየተጋፋ ነው፡፡ይሄ ለመድረክም ሆነ ለሰማያዊ በተደጋጋሚ ሲደርስባቸው የነበረ መንግስታዊ ውንብድና መሆኑ የሚያውቁት ነው፡፡ አሁን ያለው የህዝብ መነሳሳት የአዲስ አበባ ሰልፍ ነዋሪው ብቻ የሚሳተፍ ሳይሆን ቀረብ ካሉ ከተሞች ጭምር ህዝቡ በነቂስ እንደሚጎርፍ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ይሄንን ወቅታዊ የህዝብ መነሳሳት እንደለመዱት ውሃ ሊደፉበት አንዴ የቦታ ለውጥ ሌላ ጊዜ ፍቃድ የለውም አባተን ጠይቁ ከንቲባውን አናግሩ በማለት የሚጫወቱትን ሸፍጥ አሁን መድረክና ሰማያዊ ሊሰብሩት የሚገባ ፈታኝ ጊዜ ነው፡፡ ከፖለቲካም አኳያ ጥቅምና ጉዳቱ መፈተሹ ጠቃሚ ነው፡፡
የህዝቡ ወቅታዊ ቁጣና መነሳሳት ጎርፍ እንዳይወስደው ጥንቃቄ በተሞላበት ቁርጠኝነት ውሳኔ መወሰን ሁለቱም ይጠበቅባቸዋል፡፡ እስከመቼ መታለል ምርጫ ካሳጡ ሰብሮ መውጣት የግድ ነው፡፡ ህጋዊ መብት መለመን ሳይሆን መንጠቅ በራሱ ድል ነው፡፡


No comments: