Tuesday, December 22, 2015

ምንም መተንፈስ አትችልም ይላል ወያኔ ለአዲስ አበባ ህዝብ - የሚሊዮኖች ድምጽ

የታህሳስ 17 ሰልፍን ወያኔ ማድረግ አትችሉም አለ።
በተለያዩ የኦሮሚያ ቦታዎች ሕዝቡ ተቃዉሞ ማሰማቱ ይታወቃል። ከዚህ ተቃዉሞ ጋርም በተገናኘ ከሶስት ሳምንታት በላይ ትልቅ አለመረጋጋት መፈጠሩንና ከአዲስ አበባ ወደ ሊሎች ቦታዎች የሚወስዱ በርካታ መንገዶች መዘጋታቸው ይታወሳል። ከአሁን ለአሁን ተቃዉሞ በአዲስ አበባና በሌሎች ቦታዎች ይነሳል በሚልም ከፍተኛ ስጋትና ዉጥረት ዉስጥ የነበሩ ወያኔዎች በሜዲያ ራሳቸዉን ግምት ዉስጥ እስኪያስገቡ ድረስ፣ጋኔን፣ አጋንትእያሉ እሰከመሰደብና እስከመዛት መድረሳቸዉንም ሁላችንም ሰምተናል።
ወደ አላስፈላጊ ግጭት ሳይኬድ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ሕዝቡ ድምጹን እንዲያሰማ በማለት፣ ሰማያዊ እና መድረክ በጋራ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተዋል። ሆኖም የሕወሃት/ደህንነት ክፍል፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ ሕገ መንግስታዊ መብት በመረግጥ፣ የአዲስ ሕዝቡ ድምጹን እንዳያሰማ እገዳ እንዳደረገ የወያኔ አንዱ ልሳን የሆነው ፋና ራዲዮ ዘግቡዋል። 
የሕወሃትን፣ የኦህደዴ የብአዴን አመታዊ ልደቶችን፣ የብሄር ብሄረሰብ ቀን የመሳሰሉት በዓሎችን በመቶ ሚሊዮን ብሮች የሚቆጠር ወጭ እያወጡ ሲደግሱ እነርሱ እንደፈለጉት ሲለፍፉና ሲቀበጣሩ፣ ሕዝቡ ግን ምንም የመተንፈስ መብት እንደሌለው በድጋሚ እየገለጹለት ነው።
የሰላም በር ሲዘጋ የአመጽ በሮች ይከፈታሉ እንደተባለው፣ ሕጋዊና ሰላማዊ በመሆነ መንገድ ሕጋዊና ሰላማዊ በሆኑ ደርጅቶች የተጠራ እንቅስቃሴ መደረግ እንደማይችል ከተነገረ፣ የሰላም በሮች ከተዘጉ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠረው የአዲስ አበባ ሕዝብ ድምጹን በተለያዩ መንገዶች ቢያሰማ፣ ወድ አላስፈላፊ ቀዉስ ዉስጥ ቢገባ፣ ለሚፈጠረው በሙሉ ተጠያቂ የሚሆኑት ወያኔዎች ራሳቸው ናቸው።
ሰማያዊ እና መድረክ በተቻለ መጠን ሕዝቡን ቁጣዉንና ብሶቱን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ይገጽል ዘንድ፣ ሃላፊነታቸው ነዉና መንገዱን ለማመቻቸት ሞክረዋል። ከዚህ በሁዋላ እጆቻቸዉን እንደ ጲላጣሶ ታጥቦ ሕዝቡ የሚያደርገዉን ከማየት ዉጭ ሌላ የሚያደረጉት ነገር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም።
ቁልፉ ከዚህ በሁዋላ ያለው ህዝቡ እጅ ነው። ሕዝቡ ራሱ በየቀበሌው መንቀሳቀስና ይሄን ስርዓት በቃኝ ማለት፣ በኦሮሚያ እንደሚደረገው ቀበሌዎች መዉረር የመሳሰሉትን ስራዎች መጀመር አለበት። ሕግ መንግስቱ ተረግጦ፣ ድምጹን የማሰማት መብቱን የነጠቁትን መንግስታዊ ወንበዴዎችን በቃችሁ ሊላቸው ይገባል። የአዲስ አበባ ህዝብ 5 እስከ 7 ሚሊዮን ይጠጋል። እንዴት ጥቂት ወንበዴዎች ያንን ሁሉ ህዝብ አስረው ሊገዙ ይችላሉ ?


No comments: