Friday, December 18, 2015

አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ዝምታውን ሰበረ

በኢትዮጵያ የፓለቲካ ታሪክ የለውጥና የዘመናዊነት ማዕከል ሆኖ በማገልገል ላይ ያለው አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ዝምታውን በመስበር በአሁኑ ሰዓት በመነቃነቅ ላይ ያገኛል። ከአራት ኪሎ ወደ ሽሮ ሜዳ የሚወስደው መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል። በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ የፌደራል ፓሊስና የመከላከያ ሰራዊት ይተራመሳል። የነፃነት፣ የፍትህ፣ የእኩልነትና የአንድነት ችቦ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ተለኮሰ። ወያኔ የማይቀረውን የውርደት ካባ ሊከናነብ ሰዓቶች እየቸኮሉ ነው። ወያኔ ህዝብን በመናቅ በየከተሞች አስገድዶ በመሰብሰብ በሆዳም ካድሬዎቹ አማካኝነት የሚያደርገው የከረፋ ወሬ መላውን ኢትዮጵያዊ ለለውጥ እየቀሰቀሰው ነው።
በስድስት ኪሎ ካምፓስ የተቀጣጠለው አሳት ወያኔን ሳያቃጥል አይጠፋም። በመሆኑም በመላው አገሪቱ የምትገኙ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች በኦሮሞና በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመቃወም ለሁለንተናዊ ነፃነት ተነሱ። ከትምህርት በፊት ነፃነት በማለት መላው የአገራችን ወጣቶች ተነሱ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
ሞት ለወያኔና ግብረ አበሮቹ
!!


No comments: