Saturday, December 19, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በእግር ብረት ታሰረው እንደሚገኙ ታወቀ

ከተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ተይዘው ባህርዳር ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ እና የሌሎች ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት በእግር ብረት ታሰረው እንደሚገኙ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ አመራሮቹና አባላት ለረዥም ጊዜ ባህርዳር ውስጥ ታስረው የቆዩ ሲሆን እንዳያመልጡ በሚል በእግር ብረት ታስረው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በእግር ብረት ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ስማቸው ማዘንጊያ፣ አዳነ አለሙ፣ ሀብታሙ ጥላሁን፣ ልዑልሰገድ አምባቸው፣ መኳንንት ፀጋዬ፣ እያዩ መጣ፣ ደስታው ምስጋናው፣ አንቲገኝ እምሬ፣ ፈንታሁን ብዙአየሁና ታዬ ደርቤ ሲሆኑ የሌሎች ፓርቲዎች አመራሮችና አባላትም በተመሳሳይ ሁኔታ ታስረው እንደሚገኙ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡


No comments: