Wednesday, August 31, 2016

የትግራይ ወጣቶች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ትእዛዝ ተሰጠ

የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ እና ከፍተኛ የህወሓት ሹማምንቶች እምነት የሚጣልባቸው የፓርቲው ወጣት አባላትን ስብስበው ጠንካራ ትእዛዝ አስተላለፉ::
"በእናቶቾቻችሁ፥ በአባቶቻችሁ፥ በእህት፥ ወንድሞቻችሁ ደምና አጥንት ማንነታቸሁ ተከብሯል:: ደርግ ወንበዴ እያለ ሲጨፈጭፈን መስዋዕትነት ከፍለን በሰላም የምትኖሩበት፥ የምትማሩበት፥ የምትሰሩበት እና በክብር ወጥታችሁ የምትገቡበት ናጽነት አግኝተናል::
አሁን ግን የጥፋት ኃይሎች በሻእቢያ እና ግብጽ በመታገዝ ደርግን መልሰው ሊያመጡብን ትግራዋይ ላይ ግልጽ ጦርነት አውጀዋል:: ስለዚህ ይህን የመመከት ኃላፊነት በእናንተ ወጣቶች ላይ ተጥሏል::
ወላጆቻችሁ ትምክህተኞችን ጠባቦችን ደምስሰው በኢትዮጵያ ሰላም ልማት እና ዲሞክራሲ አንዳሰፈኑት ሁሉ እናንተም አኩሪውን ታሪክ የመድገም ግዴታ አለባችሁ:: አለበለዚያ የተጋሩ ህልውና አደጋ ላይ ይወድቃል ብሎም ከላይ የሻእቢያ ከታች የትምክህተኞች ጥቃት መፈንጫ ሆኖ እንደ ሕዝብ የመቀጠል እድል የማይታሰብ ይሆናል:: በተለይ አሁኑ ሰዓት በአማራ ክልል ሁከት በተጋሩ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ይህንኑ ያመላክታል::
ይህን አውቃችሁ ህወሓትንም ትግራይንም ከጥፋት በማዳን የተጋሩን ቀጣይነት አረጋገጡ:: ባለራዕዩ መሪያችን መለስ ዜናዊ የጣለብንን አደራ እንወጣ::በእናንተ ፍጹም እምነት አለን::"
በትላንትናው ዕለት ገዢው ስርዓት በግልጽ አማራ ክልል በወታደራዊ እዝ ስር እንደሚሆን በመግለፅ በከባድ መሳሪያ የታገዘ መከላከያ ሰራዊት ወደስፍራው አሰማርቷል ::
ኦሮሚያ ክልል አብዛኛው ክፍሉ በህወሓት ሰራዊት የታጠረ መሆኑ ይታወቃል::
የህወሓት ትእዛዝ ፈጻሚ የሆነው ብአዴን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አያፈነገጠ በመምጣቱ እና ሕዝባዊ ንቅናቄው ላይ የሚጠበቀውን የኃይል እርምጃ ባለመወሰዱ በኦህዴድ አመራሮች ላይ እንደደረሰው የመባረር እጣ የሚገጥማቸው ባለስልጣናት ይኖራሉ:: በተጨማሪ የብአዴን እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ በህወሀት ቁጥጥር ስር ይሆናል::

Kassa Hun Yilma

No comments: