Wednesday, August 10, 2016

የህወሃት/ኢህአዴግ የስልጣን መሰረት ተናግቷል ተባለ

አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ መንግስት መንበረ-ስልጣኑን ላይ ከተቆናጠጠ 25 ዓመት ወዲህ በቅርቡ ያጋጠመውን አይነት ህዝባዊ ተቃውሞ አጋጥሞት እንደማያውቅና፣ ይህ የተቀጣጠለው ህዝባዊ እምቢተኝነትም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል ተገለጸ።

የወቅቱን የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ሁኔታ አስመልክቶ የምስራቅ አፍሪካ ተማራማሪ የሆኑት ሬኔ ላፎትን ለዣጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) ሲናገሩኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ወጀብ ውስጥ የምትጓዝ አውሮፕላን ትመስላለችሲሉ ኢትዮጵያ ያለችበትን የፖለቲካ ቀውስ ደረጃን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የአፈና ድርጊቱን አጠናክሮ ቢቀጥልም፣ በአማራና ኦሮሚያ ተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ግን የበለጠ እያንሰራራና እየተጠናከረ እንደሆነ የገለጹት ላፎርትየተፈጠረው ቀውስ 25 አመት በፊት የነገሰውን የኢትዮጵያ መንግስት መሰረቱን አናግቶታልሲሉ ሚስተር ላፎርት አክለው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎት የተለያየ ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹት ሬኔ ላፎርት፣ ህዝቡ አሁን በስልጣን ላይ ላሉት የኢትዮጵያ መሪዎች ያላቸው ተቃውሞ ለህዝባዊ እምቢተኝነትና ለህዝቦች ትብብር መጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል ብለዋል።

አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ትውልዳቸው ከወላይታ ብሄረሰብ ቢሆንም፣ የወታደራዊና ጸጥታ ሃይሉን እንዲሁም ኢኮኖሚውን በሚቆጣጠሩ ከትግራይ በመጡ ሰዎች እንደተከበቡ የገለጸው አዣጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የሃይለማሪያም ደሳለኝን ውሳኔ ሰጪነት አቅም በጥርጣሬ አይቶታል።

ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያን ያናገረው ይኸው የዜና አውታር፣ በአናሳ ጎሳ የሚመራ የኢትዮጵያ መንግስት በብዙሃን ላይ ጫና ለመፍጠር እየሞከረ እንደሆነ መናገራቸውን አስፍሯል።መንግስት ከብዙሃኑ ህዝብ ጋር ምንም አይነት መሰረታዊ ንግግር አላደረገም ያሉት ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ፣ የህዝቡ ንዴት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ወደኋላ መመለስም የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷልሲሉ አዣጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያዊያን ለዘጠኝ ወራት ህዝባዊ ተቃውሞውን ሲያካሄዱ እንደቆዩ የተናገሩት / መረራ በበኩላቸው፣ ህዝባዊ ተቃውሞው እንደማይበርድ ለዜና ወኪሉ ተናግረዋል።የተያያዝነው ህዝባዊ አመጽ ነውማለታቸውም ታውቋል።

ህዝባዊ ተቃውሞውን አስመልክቶ የአውሮፓ ህብረት ዲፕሎማት አስተያየት ያሰፈረው አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ፣የኢትዮጵያ መሪዎች የመለስ ራዕይ ጠፍቶባቸዋል፣ የመደነባበር ባህሪይ ይታይባቸዋልማለታቸውን አስፍሯል። ስማቸው ያልተገለጸው እኚሁ ዲፕሎማት፣ የአሁኑ የኢትዮጵያ መሪዎቹ በህዝቦቻቸው ላይ ምንም አይነት እምነት አይጣልባቸውም ሲሉም ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ገልጸዋል።
ኢሳት


No comments: