Thursday, August 4, 2016

በወልቃይት ጠገዴ ጥያቄ ዙሪያ የአመራር ክፍፍል መኖሩን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ

ሐምሌ  ፳፯ ( ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- /ሚኒስትሩ በባህርዳር በመካሄድ ላይ ባለው የዲያስፖራ ውይይት ላይ   የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጥያቄ ህዝባዊነት የሌለውና አመራሮች የሃሳብ ልዩነት የመጣ መሆኑን በመግለጽ መፍትሄውም አመራሩን ማስተካከል ነው ብለዋል።
/ሚኒስትሩ የትኛው አመራር ምን አይነት አቋም እያራመደ እንደሆነ ከመገልጽ ቢቆጠቡም፣ ከዚህ በፊት በተወሰኑ ከፍተኛ የብአዴን አመራሮችና በህወሃት አመራሮች መካከል ልዩነት መፈጠሩ ሲነገር የነበረውን የሚያረጋግጥ ሆኗል። አቶ ሃይለማርያም የወልቃይት ጠገዴን የአማራ ማንነት ጥያቄ ውድቅ ሲያደርጉት የብአዴን ከፍተኛ አመራርና የፌደራል ጉዳዮችና የአርብቶ አደሮች ሚኒስትር የሆኑት ካሳ ተክለብርሃን የወልቃይት አማራ ተወላጆች በትግራይ ክልል መሬት ላይ ሄደው ሰፈሩ እንጅ የትግራይ ተወላጆች በወልቃይት አማራ መሬት ላይ አልሰፈሩም በማለት የወልቃይት ጠገዴን ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል።
በገዢው ፓርቲ በኩል የተያዘው አቋም፣ የአማራ ክልል ህዝብ ከያዘው አቋም ጋር የሚጋጭ መሆኑ፣ የተወሰኑ የክልሉን አመራሮች ከሃላፊነት በማንሳትም እንኳ የማይበርድ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። የፌታችን እሁድ በባህርዳር እና በደብረታቦር ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ ይደረጋል። የጥሪ ወረቀቶች በየቦታው እየተበተኑ ሲሆን ወጣቶች የቅስቀሳ ስራዎችንም እየሰሩ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ የፌደራሉ የጸረ ሽብር ግብረሃይል ሃምሌ 5 ቀን በጎንደር ተካሂዶ በነበረው ተቃውሞ የትግራይ ነጋዴዎችና ነዋሪዎች ኢላማ ተደርገዋል በሚል ያወጣውን መግለጫ የአማራ ክልል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል። የጸረ ሽብር ግብረሃይልና የህወሃት ደጋፊዎች የትግራይ ሰዎች ጎንደር ውስጥ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል በማለት ተቃውሞው የብሄር ቅርጽ እንዲይዝ ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደር ቆይተዋል። የክልሉ መንግስትም የትግራይን ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ በማስወጣት ጉዳዩ የዘር ግጭት ቅርጽ እንዲይዝ ለማድረግ ሙከራ ሲያደርግ ቆይቷል።
አቶ ንጉሱ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ግን  በጎንደር ከወደሙት ንብረቶች መካከል  የአማራ 85 የትግራይ 30 ቀሪው ደግሞ የሌሎች ብሔር ተወላጆች ንብረት መሆኑን በማረጋገጥ የትግራይ ተወላጆች በተለዬ ጥቃት እንዳልደረሰባቸው በመግልጽ በመንግስት የቴሌቪዥን ጣቢያ  ወይም ኢቢሲ) የተላለፈውን መግለጫ ውድቅ አድርገውታል።
የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት የኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ ክስ እንደተመሰረተባቸው ይታወቀ ሲሆን፣ / ደመቀ ዘውዴን ለመውሰድም እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። / ደመቀ ከክልሉ ውጭ የትም መሄድ እንደማይፈልጉ፣ በተለይ የአገር ሽማግሌዎች ቃላቸውን አክብረው ከታገቱበት እንዲያስለቅቁዋቸው ጥሪያቸውን እያቀረቡ ነው። የሰሜን ጎንደር ህዝብ ኮሎኔል ደመቀ ተላልፈው እንዳይሰጡ ሲያስጠነቅቅ ቆይቷል።


No comments: