አምናና ዘንድሮ፣
ከፍተኛ እርዳታ ካገኙ
ሦስት አገራት
አንዷ ኢትዮጵያ
ናት።
ለረሃቡ 1.4 ቢ ዶላር (30 ቢ. ብር) እርዳታ ተገኝቷል። ግማሹ ከአሜሪካ! (የዩኤን መረጃ)፡፡
3ቱ ትልልቅ ለጋሾች፣ የአሜሪካ፣ የእንግሊዝና የጀርመን መንግስታት ናቸው።
ረሃብ የሚከሰተው፣ የእህል ምርት ምን ያህል ሲቀንስ ነው?
በ1966 ዓ.ም፣ የእህል ምርት 13 ሚ. ኩንታል ቀንሶ ነበር። በ77ም እንዲሁ
(የዓለም ባንክመረጃ)፡፡
በ2007 ዓ.ም? ረሃብ የተከሰተው፣ የእህል ምርት በ5ሚ ኩንታል ስለቀነሰ ነው። (ስታትስቲክስ ኤጀንሲ)።
አዴግ ሰሞኑን ያወጣውን ረዥም መግለጫ ሰምታችኋል? ከመግለጫው ውስጥ ጥቂት ዓረፍተ ነገሮችን በመመልከት፣ የአገራችን ፖለቲካ ምን እንደሚመስል መታዘብ እንችላለን። እንደተለመደው፣ እንደወትሮው፣ ተቃዋሚም፣ ደጋፊም እንደሚያደርገው፣ ለፕሮፓጋንዳ እስከጠቀመ ድረስ፣ ፍሬ እና ገለባውን እያደበላለቁ የመንጎድ ፖለቲካ፣ የአገራችን ባህል ነው፡፡
በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ኃይለኛ ድርቅ መከሰቱን ይጠቅሳል መግለጫው። ከዚያስ? “ትርጉም ያለው እርዳታ” ባናገኝም፤ የረሃብ አደጋውን በራሳችን አቅም መቋቋም ችለናል ብሏል ኢህአዴግ፡፡ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ስለተሻሻለ የረሃብ አደጋው እጅግ የከፋ ጥፋት እንዳላደረሰም ተናግሯል፡፡
እስቲ፣ እውነተኛውን መረጃ … እውነተኛውን ፍሬ ከገለባው ለመለየት እንሞክር፡፡ አዎ፣ የአምናው ድርቅ፣ ባለፉት 50 ዓመታት ከተከሰቱት የዝናብ እጥረት አደጋዎች ሁሉ የከፋ እንደሆነ አለማቀፍ የሙያ ተቋማት ገልፀዋል። በዚሁ ድርቅ ሳቢያ ብዙ ሰው በረሃብ አለማለቁም፣ ደግ ነገር ነው፡፡ “ትርጉም ያለው እርዳታ አላገኘንም” የሚለው የኢህአዴግ አባባል ግን፣ ፍሬ የሌለው ገለባ ነው። ደግሞም ያስተዛዝባል። ዘንድሮ፣ ከሶሪያ በመቀጠል፣ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የነፍስ አድን እርዳታ አግኝታለች፡፡ ይሄ፣ ትርጉም የለውም?
በደፈናው ሳይሆን፣ በቁጥር ቁልጭ ብሎ ይታያልኮ። ኢትዮጵያ፣ ባለፉት ሃያ ወራት ብቻ 1.4 ቢሊዮን ዶላር (30 ቢ. ብር) ነፍስ አድን እርዳታ እንዳገኘች የዩኤን መረጃ ይገልፃል፡፡
ይሄ ቀላል እርዳታ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ እስከዛሬ ካገኘችው የረሃብ እርዳታ ሁሉ ይበልጣል፡፡ ያው፣ እንደሌላው ጊዜ፣ ዋናዋዎቹ ለጋሾች፣ የአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት ናቸው - በተለይም የአሜሪካ መንግስት፡፡ ከጠቅላላው እርዳታ ውስጥ፣ ግማሹ ከአሜሪካ መንግሥት የተሰጠ ነው - 684 ሚሊዮን ዶላር (15 ቢሊዮን ብር ገደማ)፡፡
ከአሜሪካ በመቀጠልስ?
በአውሮፓ ህብረት በኩልና በተናጠል በሚሰጡት እርዳታ፣ የእንግሊዝና የጀርመን መንግስታት ይጠቀሳሉ። እያንዳንዳቸው ከ140 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለረሃቡ ለግሰዋል፡፡
እነዚህን እውነታዎች መካድ፣ ያስተዛዝባል፡፡ ምስጋና ቢስ መሆን ምን ጥቅም አለው? በእርግጥ፣ “እርዳታ መገኘቱ በቂ ነው” ማለት አይደለም፡፡
እርዳታው በጊዜ ካልደረሰና በወጉ ካልተሰራጨ፣ ብዙ ጥፋት ይከሰታል፡፡ የእርዳታ እህል ደግሞ፣ ቶሎ አይደርስም፡፡ እናም፣ መንግስት ቀደም ብሎ፣ እህል ገዝቶ ማምጣቱ ጥሩ ነው፡፡ ወጪውን በእርዳታ ያካክሳል፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፡፡ መንግስት፣ በየመስኩ ሲዝረከረክና ችግሮች ሲያባብስ እንደምናየው፣ የእርዳታ ስርጭት ላይ ቢዝረከረክ ኖሮ ብዙ ጥፋት በደረሰ ነበር። ይህ አለመሆኑ መልካም ነው። ምን ለማለት ነው? ከፍተኛ እርዳታ መገኘቱን መካድ ሳያስፈልገው፣ “እኔም አደጋውን ለመቋቋም ጥሬያለሁ” ማለት ይችል ነበር፡፡ ፍሬውን ከገለባው መለየት ከጀመርን? “የአገሪቱ ኢኮኖሚ ስለተሻሻለ፣ የረሃብ አደጋው የከፋ አደጋ አላደረሰም” የሚለውን አባባል ደግ እንይ፡፡ የእህል ምርት አድጓል ማለት ነው፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? የእህል ምርት ካላደገማ በረሃብ እናልቃለን፡፡ በሃያ ዓመት ውስጥኮ፣ የአገሪቱ የህዝብ ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል፡፡ የእህል ምርት ካላደገ፣ በእርዳታም መዳን አይቻልም፡፡ ይልቅስ፣ ዋናው ጥያቄ፣ “የእህል ምርት በምን ያህል መጠንና በምን ያህል ፍጥነት አደገ?” የሚል ነው፡፡
የእህል ምርትን ከህዝብ ብዛት ጋር ማገናዘብ እንችላልን፡፡ ከ1950 ዓ.ም ጀምሮ፣ ንጉሱ እስከወረዱበት ድረስ የተመረተውን የእህል ምርት እንመልክት፡፡
የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ያኔ በየዓመቱ በአማካይ፣ ለአንድ ሰው 180 ኪሎ እህል ይመረት ነበር፡፡ ለሃያ ዓመታት፣ እስከ 1966 ዓ.ም ድረስ፣ እንዲህ ነበር የቀጠለው፡፡ ንጉሱ እስከወረዱበት ዓመት ድረስ ማለት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ግን፣ ማሽቆልቆል ጀመረ። በደርግ ዘመን፣ አመታዊው የእህል ምርት፣ ለአንድ ሰው ከ140 ኪሎ ግራም በታች ነበር ይላል መረጃው፡፡ በኢህአዴግ ዘመንም ቶሎ አልተሻሻለም፡፡ የእህል ምርት በንጉሱ ዘመን ወደነበረበት ደረጃ የተሻሻለው፣ በ2002 ዓ.ም ነው፡፡
ምን ማለት ነው? “የእህል ምርት አድጓል” ተብሎ ሲነገር፤ “አገሬው አለፈለት፤ በለፀገ፤ ተትረፈረፈ” ማለት አይደለም፡፡ “ከ35 ዓመታት በፊት ወደነበረበት የምርት ደረጃ ተሻሽሏል” እንደማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር፣ ያው፣ … እንደያኔው፣ ዛሬም ድህነት ውስጥ ነን፡፡ እንደያኔው ዛሬም፣ ለድርቅ እና ለረሃብ በጣም ቅርብ ነን፡፡ አፋፍ ላይ ነን ከታች ገደል፣ ከላይ ናዳ፡፡

addisadmassnews
No comments:
Post a Comment