Thursday, August 4, 2016

“ዛሬ ዮናታን ተስፋዬ አቃቢ ህግ ባቀረበበት ሰነዶች ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ነበረው።

ዛሬ ዮናታን ተስፋዬ አቃቢ ህግ ባቀረበበት ሰነዶች ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ነበረው። በፀረሽብር አዋጁ አንቀፅ 4 የቀረበበት ክስ ተቀይሮ በፀረሽብር ህጉ አንቀፅ 6 (ሽብርተኝነትን ማበረታታት) ስር እንዲከላከል ብይን ተሰጥቷል። በማስረጃነት ከተያያዙበት 9 የፌስቡክ ስታተሶቹ መሃል 6 ናቸውሽብርተኛነትን ያበረታታሉየተባሉት። ሽብርተኝነትን ያበረታታሉ ከተባሉት ስታተሶች ውስጥ ህዳር 24 2008 ላይ የፃፈውን ~ “ህግ መጨቆኛ መሳሪያ ሲሆን አመፅ የህሊና ህግ ይሆናልየሚለውን ዳኛው በችሎቱ ላይ ሁለት ጊዜ ሲጠቅሰው ተሰምቷል። ዮናታን የሰውና የመከላከያ ምስክሮቹን እንዲያቀርብ ከጥቅምት 14 -16 2009 ቀጠሮ ተሰጥቷል።ተብሏል።
እንግዲህ ህጉ እንዲህ የተዝረከረከበት ሁኔታ ነው ያለው። (የዛሬ 15 ቀን ገደማ “16 ዳኞች ለጠቅላይ /ቤት በተወካዮች /ቤት ተሾሙየሚል ወሬ ሰምቼእንዴት ነው ይኼ የዳኞች ሹመት አልበዛም? እስኪ መጀመሪያ /ቤቶች በገለልተኝነት ለፍትህ ይቁሙ! “ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ቁጢጥስል የወቀሳችሁኝ ወዳጆች በተለይ አስተውሉት።)
ህግ መጨቆኛ መሳሪያ ሲሆን አመጽ የህሊና ህግ ይሆናል።የሚለው እኮ የተፈጥሮ ህግ እና እውነት እንጂ ሌላ ነገር አይደለም። አሁንስ በየቦታው እየሆነ ያለው ምንድን ነው? በህግ የተጨቆኑ ድምጾች በህሊና ህግ ተመርተው እየተነፈሱ አይደለምን? የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ተናግሮት እንደነበረው “Those who make peaceful revolution impossible, will make violent revolution inevitable” ነው ነገሩ።
አቃቤ ህግ ክሱን ማሰናዳቱ ከባህሪያቸው የተነሳ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በጣም የሚያሳፍረው ዳኛው ይህንን እንደቁም ነገር እና እንደ ውሸት መደጋገሙ ነው። ህጉን መጨቆኛ መሳሪያ እንዳይሆን የህሊናቸውን ህግ አክብረው ይኑሩ!


No comments: