Thursday, August 18, 2016

ወልቃይትን ለባለቤቱ ህዝብ ለመመለስ ህወሃት እየመከረ ነው

ህወሃት ግድያ እንዲያቆም ከጌቶቹ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጠው
ethiopia police soilders
* “ብልጡን ባለ ራዕይ መሪክፉኛ ናፍቋል!
የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር /ህወሃት/ አመራሮች ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ከመግደልና ከማስገደልእንዲታቀቡ ታዘዋል። ግድያው የሚቀጥል ከሆነ ከወትሮው በተለየ ርምጃ እንደሚወሰድ ተነግሯቸዋል።ወልቃይትን ለባለቤቱ ህዝብ ብንመልስ ይሻላልበሚሉናአንመልስምሲሉ በሚቃወሙ መካከል ክርክር የጀመረው ህወሃት ስምምነት ሊደርስ አልቻለም። ሁኔታው መለስን ከመቃብር ቀስቅሷል።
አባይ ጸሃዬ፣ ሳሞራ የኑስና ሌሎች ባለስልጣናት አሜሪካ እንደነበሩ ለጎልጉል ጠቁመው የነበሩት የመረጃው ምንጮች እንዳሉት ባለስልጣናቱ ግድያ እንዲያስቆሙ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ተቀብለዋል። በአማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ ያሳሰበው ህወሃት በተመሳሳይ አሜሪካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጡ ጫና እንድታደርግ ጠይቀዋል። ለዚህም ይመስላል በአሜሪካ በኩል የተቀናቃኝ ድርጅት መሪዎችን በተናጠል ማነጋገር ተጀምሯል።
ህወሃት በግድያው ከገፋበት ከአሜሪካ በኩል የሚሰጠው ምላሽ እንደ ወትሮው በኤምባሲ ወይም በህዝብ ግንኙነት በኩል እንደተለመደውጉዳዩ አሳስቦናልየሚል ተራ መግለጫ እንደማይሆን ማረጋገጫ መሰጠቱን ጎልጉል የሚያምናቸው የዲፕሎማት ምንጮች ከአሜሪካ ተናግረዋል። እንድ መረጃ አቅራቢዎቹ ቀጣዩ የአሜሪካ አቋም በውጭ ጉዳይ /ቤቱ (ስቴት ዲፓርትመንት) ዋና ኃላፊ ወይም ከፕሬዚዳንቱ /ቤት (ኋይት ሃውስ) በኩል የሚተላለፍ እንደሚሆን ይጠበቃል። ባለፉት ሳምንታት ግማሽ ያህል የህወሃት ባለስልጣናት አሜሪካ ደርሰው መመለሳቸውን ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑ ሌላ ዜናን ለማስተባበል ሲሞክሩ ሳያስቡት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
በሌላ ዜና በህወሃት ውስጥወልቃይትን መመለስ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነውበሚሉናሊመለስ አይገባምበሚል የሃሳብ ልዩነት መፈጠሩ ታውቋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው በዚሁ ጉዳይ የተሰየመው የህወሃት አመራሮች ስብሰባ ለቀናት ቢወያይም ስምምነት ላይ ሊደርስ ግን አልቻለም።
ወልቃይትን እንመልስባዮቹ ወገኖች አማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ አስፈሪ፣ የከረረ፣ እስከወዲያኛው ለስልጣናችን የሚያሰጋ ስለሆነ ወልቃይትን መልሶ አገሪቱን ማረጋጋት የግድ ነው ይላሉ።ወልቃይትን መመለስ የለብንም፣ እንዴት ተደርጎስ ይመለሳል? ውርደት ነውበሚል አቋም የያዙት ደግሞ ሁለት መከራከሪያ አላቸው።
እንደ ዘጋቢያችን መረጃ ከሆነ እነዚህ ክፍሎች ሁለት ነጥቦችን በማቅረብ የተከራከሩትአንመልስም፣ ከመለስንም መሰረተ ልማቱንና ያፈራነውን ሃብት ምን እናደርገዋለን?” በሚል ጥያቄዎች የታጀቡ ናቸው።
ወልቃይት የኖሩት ወገኖቻቸን ሃብት አፍርተዋል። ለማን ነው ጥለውት የሚሄዱት?” የሚሉት እነዚህ ወገኖች አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ/ሃይል በመጠቀም በተጀመረው መንገድ መቀጠል እንዳለበት የሚመኙ ሲሆኑ፣ ምኞታቸው ካልተሳካ መሰረተ ልማቱን በሙሉማፈራረስ ሌላው የመጨረሻ ውሳኔያቸው ነው።
በዚህ ሁለት ሃሳብ የሚነታረከው የህወሃት አመራሮች ስብሰባ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ዕለት ድረስ ከውሳኔ ላይ አልደረሰም። ይሁንና በዚህ ውሳኔ ላይ እንደ ከዳ የሚነገርለት ብአዴን አቋሙ እንዲጠየቅ አልተደረገም።
ህወሃት ለረጅም ዓመታት በተለያዩ መንገዶች ሲያፍን የቆየው የሕዝብ ዓመጽ በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች መፈንዳቱ ሥርዓቱን ክፉኛ አናግቶታል፡፡ በፓርቲ ወይም በድርጅት ሳይመራ በሕዝብ እምቢተኝነት የገነፈለው ተቃውሞ በስልትና በግለት እየጠነከረ መምጣቱ ህወሃት የመግደል እርምጃ እንዲወስድና ከምዕራባዊ ጌቶቹ ጋር እንዲቃቃር እያደረገው ነው፡፡ በሥልጣን መቆየት በአንድ በኩል፤ በሌላ ደግሞ ከምዕራባውያን ጋር ስሙም መሆን የወጠረው ህወሃት ከዓቅሙ በላይ የሆነው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ከቀን ወደ ቀን እያየለበት በንጹሃን ላይ ጥይት መተኮሱን አላቆመም፡፡
ይህ አካሄድ ህወሃትን ለክፍፍል እንደሚዳርገው ከተለያየ አቅጣጫ ይነገራል፡፡ ለዘመናት ህወሃትን ስትንከባከብ samantha powerየነበረችው አሜሪካ በተወሰነ መልኩ ጉዳዩን የማክረር ሁኔታ ይታይባታል፡፡ የአሜሪካንን ፖሊሲ የማስቀየር አቅም ያላቸው ጋዜጦች ኢትዮጵያ በአናሳዎች የምትመራ ከዴሞክራሲ የራቀች አገር መሆኗን እንደ አዲስ ለፖለቲከኞቻቸው እያስተዋወቁ ነው፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ነጻ አካል ምርመራ እንዲደረግ የተደረገውን ውሳኔ ህወሃት አልቀበልም ባለ ወቅት በመንግሥታቱ ማኅበር የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ሰማንታ ፓወር ህወሃትነጻ ምርመራውን መቀበል አለበትበማለት በትዊተር የከረረ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
መጪው ጊዜ የከፋ እንደሚሆን የገመቱ፣ ለዘብተኛ ለመሆን የሚፈልጉና በሃብት የደለቡ የህወሃት ሰዎችና አሽከሮቻቸውበጥገናዊ ለውጥሁኔታዎች እንዲረግቡ ይፈልጋሉ፡፡ ምዕራባዊ አገራት በመቆየት ዘምነናል የሚሉና የምዕራባውያን ድጋፍ እንዳላቸው በተለያየ መልኩ የሚጠቅሱት በዚህ ውስጥ ይካተታሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ህወሃት/ኢህአዴግ ከየቦታው የሰበሰባቸውና በየአገሩ ተወካይ (አምባሳደር) አድርጎ ያስቀመጣቸው ተላላኪዎቹም ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ክፍሎች በራሱ በህወሃት ከረከሰው ሽምግልና እስከ ዕርቅ ለመሄድ የሚጥሩትንም ይጨምራል፡፡ ብንከስርም ወልቃይትን ለባለቤቱ እንመልስ ባዮቹ የዚህ ዓላማ አራማጆች ናቸው፡፡ የነዚህ ተቃራኒዎች ማሸበርና መግደል በመቀጠልካልገዛን እንሞታለንብለው ህወሃትን ከጌቶቹ ከማቃቃር እስከአሜሪካ ከከፋት ጉዞ ወደ ቻይናየሚሉ የተሰባሰቡበት ነው፡፡ የበረሃ ገድላቸውን እየጠቀሱደጋፊዎቻቸውጠብመንጃ እንዲወለውሉ የሚቀሰቅሱናሪፓብሊካቸውንበአየር ኃይል ጭምር ለመከላከል የወሰኑ በዚህ ምድብ ውስጥ ተከማችተዋል፡፡
የእነዚህና ሌሎች ኃይላት ትንቅንቅ ህወሃትን አደገኛ ፈተና ውስጥ እንደጣለው ይነገራል፡፡ አራት ዓመታት በሙት መንፈስና ሌጋሲ ሲመራ የቆየው ህወሃት/ኢህአዴግ ታዛዥነት፣ መደማመጥናብልጠትጠፍቶበትባለ ራዕይ መሪውንክፉኛ ናፍቋል፡፡
Source: goolgule


No comments: