Friday, August 5, 2016

በሻሸመኔ ተቃውሞው ተጀመረ

shashemene
(-ሐበሻ) በሻሸመኔ ከተማ ሕዝብ ወደ አደባባይ እየወጣ መሆኑ ተሰማ:: በመላው ኦሮሚያ ዛሬ የተጠራው ሕዝባዊ ተቃውሞን ለማፈን መንግስት ሶሻል ሚድያዎችን በመዝጋት ለማፈን ቢሞክርም ሕዝብ በየከተማው እየተሰባሰበ መሆኑ ተሰምቷል::
ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው በሻሸመኔ በአሁኑ ወቅት ቁጥሩ በርካታ የሆነ ሕዝብ መፈክሮችን ይዞ በመውጣት አደባባይ ላይ ተቃውሞውን እየገለጸ ነው::
በሻሸመኔ እየተደረገ ባለው ተቃውሞ እየተሰሙ ካሉ መፈክሮች መካከል የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ; ወልቃይት አማራ ነው; በኦሮሚያ ግድያ ይቁም የታሰሩ የሙስሊም ወኪሎች ይፈቱ እናም ሌሎች ይገኙበታል::

የሕወሓት ሰራዊት በሻሸመኔ ከተማ ስናይፐሮችን እና ከባድ የጦር መሳሪያዎችን አቁሙ ሕዝቡን ለማስፈራራት ቢሞክርም ተቃውሞው ግን እንደቀጠለ ነው::
ዝርዝር መረጃዎችን እየተከታተልን እናደርሳለን::


No comments: