Tuesday, August 9, 2016

ይህ ሁሉ ደም እያፈሰሰ ያለው ያለ ህዝብ ይሁንታ ረግጦ ለመግዛት ነው።

የኢትዮጵያ መሬት በደም አጨማልቆ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ሕወሃት/ኢህአዴግ/ወያኔ ስልጣን ላይ መቆየት የለበትም። ይህ ሁሉ ደም እያፈሰሰ ያለው ያለ ህዝብ ይሁንታ ረግጦ ለመግዛት ነው። ህዝብ እንቢ በቃኝ ብሏል። እጃቸው በደም ለዛውም በንፁሃን ኢትዮጵያውያን ደም በተጨማለቀ በወያኔ ኢሃዴጋውያን መመራት አልፈልግም እስካለ ድረስ መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል።
ከዚህ በኋላ ድርድር ሳይሆን ወያኔ/ኢህአዴግ ባስቸኳይ ስልጣን ለህዝብ ማስረከብ አለበት። አሁን በያዘው አቋም ከቀጠለ ደግሞ ትግላችን በተጀመረው መሰረት በማጠናከር የሚከፈለው መስዋዕትነት ከፍለን ህዝብ የስልጣን ባለቤት እስኪሆን ድረስ መታገል ይኖርብናል።
የድል ቀን ቅርብ ነች!
ለነፃነታችን በጋራ፣ በህብረት፣ በአንድነት እንታገል!
ለትግል ተነሱ!


No comments: