Source: Facebook, welkait.com
በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ የታቀደው ድቡቁ የህወሓት ሴራ ሲጋለጥ
በቅድሚያ ይህንን ድብቅ የወያኔን ሴራ የሚያጋልጠውን ሰነድ ከነትርጉሙ ለላኩልን
ወገኖቻችን ከልብ እናመሰግናል። መጋቢት 2008 ዓ.ም
ከዚህ በታች የምታነቡት በትግረኛ ተጽፎ የህወሓት ባለስልጣናት የተወያዩበትና የተስማሙበት ድብቅ መረጃ ነው። ይህ ረቂቅ ዶኩመንት በወያኔም ባለስልጣናት ተቀባይነት አግኝቶና ጸድቆ በተግባር በአስቸኳይ በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ በተግባር ላይ እንዲውል ስምምነት ተደርሶበታል።
ይህ በትግረኛ የተዘጋጀውና ወደ አማርኛ የተተረጎመው ሰንድ የተዘጋጀውና በህወሃት ባለስልጣናት እንዲተገበር ያቀረበው በብዕር ስሙ ዘጽኣት አናንያ በሚል ስም የሚታወቅ እውነትኛ ስሙ ግን ጎይቶኦም የማነ ገብረኣናንያ የተባለ ቀንደኛ የህወሃት ስውር ፊታውራሪ ነው።
ከትግረኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመውን ከዚህ ቀጥሎ ያንብቡ። በትግረኛ የተጻፈው በመጨረሻዎቹ 3 ገጾች ላይ ማንበብ ይቻላል።
********************************************************************************************
ባለፉት 15 ኣመታት በትንሽ ግለሰቦች ሲነሳ የቆየ ባሳለፍናቸው ትንሽ ኣመታት ደግሞ የተቃውሞ ቅርፅ እየያዘ እየመጣ ያለው በምዕራባዊ ዞን ወረዳ ጠለምትና ግላዊ ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለሰቦች በኣሜሪካ በሚገኙት የሰሜን ጎንደር ወልቃይት ጠገዴ እድርና በጎንደር ህብረት በሚባሉ የስምሪት ኣሰላለፍ እየተረዱ ይመለከተናል በሚሉት የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ኣካባቢ እጆጃቸው ለኣንዳችም የልማት ስራ እንኳ ሳያነሱ ለነዚያ የግል ቅሬታ ያለባቸው ሰዎች በማሰባብሰብ የገንዘብ፣ የሞራልና ሓሳብ ምክር ሙሉ ድጋፍ በመስጠት ለኣራቱም የትግራይ ወረዳዎች ነዋሪዎች የኣማራ ማንነት ጥያቄ እንዳላቸውና በማንነታቸው ወደ ሚመስላቸው የኣማራ ማንነት ሊመለሱ እንደሚፈልጉ በማስመሰል ህዝብ ያልጠየቀው ጥያቄ በመያዝ ከህግ ውጭ የማንነት ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ፌደረሽን ምክር ቤት፣ የኣማራ ክልል ርዕሰ ኣስተዳደርና ሌሎች የፌደራል ኣካላቶች እንደደረሳቸው በተለያየ መልክ ተሰራጭቷል።
ይህ ጉዳይ ሕጋዊ ለማስመሰልና ለማሰራጨት ሰንደቅ ጋዜጣ በ28 ቀን 2008 ዓ/ም ዕትም ኣድምቆ ለማቅረብ ሞክሯል። ከዚህ በተጨማሪ በትምክህተኞች ሃይል የሚመሩ ሚዲያዎች እየተሰራጨና እየተስፋፋ መጥቷል ፤ እየመጣም ነው። ከዚህ በመሻገር ደግሞ በውጭ ከሚገኙ ሚሊዮን ዶላሮች ለዚህ ኣላማ ለማዋጣት ዝግጁነታቸው በማጠናቀቅ ለጦርነት እስከ የማነሳሳት ስራ ለመስራትና ከጎጃምና ኣብዛኞቹ የጎንደር ወረዳዎች የገንዘብ እርዳታ የሚደረግላቸው በቀን ሰራተኛነት ስም ወደ ምዕራባዊው የትግራይ ዞን (ወልቃይት፣ጠገዴ፣ ቃብቲያና ሁመራ) በብዛት በማስገባት ኗሪ ለማድረግ በተዘጋጁብት ግዜ እና ከኣማራ ክልል ኗሪ ለዚህ እንቅስቃሴ ለመደገፍ ከጎናቸው በቆሙበት ስኣትና በትንሽ የብኣዴን ኣመራር ካድሬዎች ኣይዟችሁ እያሉ ባሉበት ስኣት ትግሬዎች እንደትግሬነታችን ተነሳስተናል ወይ የሚል ጥያቄ እንድታነሳ ያድርጋል። የዚህ ምልክት
በዚህ ሳምንት በፌስቡክ የተለቀቀው የ13 ደቂቃ የቅስቀሳ ቪድዮ በቋራ ይካሔድ ወይንስ በኣርማጭሆ ብዙ ሰው በተገኘበት ዳስ ተጥሎ የመብልና የመጠጥ ግብዣ ተደርጎ ቅስቀሳ ሲደረግ ከላይ ያለውም ሆነ ታችኛው የብአዴን ኣመራር ኣያውቅም ማለት የዋህነት ነው።
ስለሆነ በትግራይስ እንደ ህወሓት ምንና ምን ስራዎች እየተሰሩ ነው የሚል የብዙ ትግሬዎች ጥያቄ እንኳን ቢሆንም በሚስጥር እየተሰራ ከሆነ ጥሩ ሆኖ ሳለ ህወሓት በመሬት ጉዳይ ተዝናንታ ስትቆይና በድረስ ድረስ
ባለቀ ስኣት ብትሯሯጥ ግብ ሳይመቱ የመቅረት የነበሩዋት ክፍተቶች ኣሁንም እንዳይከሰት እንድትጠራጠር ያደርግሃል። ይህ በኢትዮጵያ የመንግስት ሽግግር ግዜ የኣማራና ትግራይ ክልል ሲከለሉ የነበረው የህወሓት ቅንነት ግን ደግሞ የብአዴን ተንኮል ታይቷል። ለምሳሌ፦ ግልፅ በሆኑ ኣከባቢዎች በግልፅ የሚወሰድ ሲሆን በእነዛ የሁለቱም ብሔረሰቦች የሚገኙበት ኣካባቢ ማለትም የትግርኛ ተናጋሪዎችና የኣገዉኛ ተናጋሪዎችም ተደበላልቀው የሚኖሩበት ከሰቆጣ እስከ ኣበርገሌ ፊናርዋ የትግርኛ ተናጋሪ ነህ ወይስ የኣገውኛ እየተባሉ በሚጠየቁበት ግዜ በብአዴን የተሸረበ ተንኮል ለሁለቱም ቋንቋ እኩል የሚችላቸውን ህዝብ ትግርኛ ትችላለህ ሆይ ተብሎ ሲጠየቅ ኣልችልም የሚል ጭንቅላቱ ነቅንቆ ምልክት ሲያሳይ በተቃራኒው ደግሞ ኣገዉኛ ትችላለህ ሆይ ተብሎ ሲጠየቅ ኣዎ ብሎ መልስ እንዲሰጥ ውስጥ ለውስጥ ተሰርቶበት በኣብዛኛዎቹ ድል ሲቀናቸው በተወሰኑ የፊናርዋ ኣካባቢና በግማሽ የኣበርገሌ ኣካባቢ ተደናቅፈው በዚህ ምክንያት ፊናርዋ ከፊል የኣበርገሌ ወደ ትግራይ ሲሆኑ እነዛ ብዙዎቹ ቀበሌዎች ግን ወደ ኣማራ እንዲከለል ተደርጓል፤ ይህ የክልሎች መነሻ ክለላ ስለነበረ ብዙ ጥያቄዎችን ኣላስነሳም። ከክልላችን ውጭ ባሉ ስንመለከት ደግሞ ከ1998 እስከ 2008 ዓ/ም የይገባኛል ጥያቄዎች የሶማሊ ክልል ከኦሮሚያ ክልል ፤ የደቡብ ክልል ከኦሮሚያ ክልል በሁለቱም በኩል ጥያቄ የተነሳበት ኣከባቢዎች በፌደረሽን ምክር ቤት ወደ ሪፈረንደም እንዲቀርብ በማድረግ ልክ ይሁን ኣይሁን እልባት
ተደርጎበታል። ለምሳሌ፦ በሶማሊና ኦሮሚያ ክልል የተነሳው የይገብኛል ጥያቄ ከመኢሶና ኣዋሽ ወንዝ ጥግ እስከ የኬንያ ኣዋሳኝ የሚዘልቅ ብዙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ያቀፈ ነበር። በዚህ ሁኔታ ሁለቱም ክልሎች ኮሚቴ ኣቋቁመው የሪፈረንደም ቀን የሚያደርስ የስብከትና ብዙ ሚሊዮን ብር በጣም ብዙ ሺ ኩንታል ስንዴ እና ሩዝ እንዲሁም ዘይት ለህዝቡ በዋነኝነት ለጎሳ መሪዎችና የኣገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ተሰሚነት ላላቸው ወገኖች ሲሰጡ ከቆዩ ብሗላ የቋንቋቸው ተናጋሪዎች እንደስጦታቸው መጠን፣እንደ ስብከታቸው፣ ተንኮላቸውና ቅልጥፍናቸው መጠን ወረዳዎችና ቀበሌዎች ኣግኝተዋል። በኦጋዴን ሰራዊት መከላከል ምክንያት ደካማ ውስጣዊ ኣሰራር የነበረውን የሶማሊ ክልል የተሻለ የኮሚቴዎች ኣወቃቀር፣ ብር፣ ስንዴና ሩዝ የነበረው
የኦሮሚያ ክልል በጣም በበለጠ ሁኔታ ድል ሊቀናው ችሏል። በኣሁኑ ስኣት ኣብዛኞቹ የሶማሊ የነበሩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በማጉረምረም ላይ ናቸው። ተታለን ወደ ኦሮሚያ ሔደን ኣሁን ልጆቻችን ቋንቋቸውን ትተው በኦሮምኛ በግድ እየተማሩ ነው፤ ያለ ቋንቋችንና ኣስተዳደራችን እየተዳደርን ነው ይላሉ። ይሁን እንጂ የማይመለስ ንስሓ መሆኑ ግን በሚገባ ተረድተዋል።
ይህ ከላይ የተገለፀው በእኛ ላይ እንዳይደገም እኛ ትግሬዎች ምን ብናደርግ ነው የሚሻለው?
የወልቃይት ጠገዴና ኣካባቢዎቹ የታወቁ የናይዝጊ ልጆች መሆናቸው ያ መሰረቱ የማይጠፋው የናይዝጊ ቤተ መንግስትና የትግርኛ ታናጋሪዎች መሆናቸውን የሚያጠያይቅ ስላልሆነ የፅሑፍ ሓተታ ኣያሰፈልገንም። ታዲያ ለምን? ቢሉ ከፊላችን እያወቅን ከፊላችን ደግሞ በየዋህነት እንዳንዘናጋ ወይ ደግሞ ብአዴን ያን ውስጣዊ የክልላዊ ስልጣን ተቀባይነቱ ለማናር ብሎ ብአዴን ህዝብ እየጠዬቀ ነው በሚል በግልፅ ጥያቄው ለፌደረሽን ምክር ቤት ሊያቀርብ ስለሚችል ሳንታለል ተዘጋጅተን መቆየት ስልያስፈልገን ነው። ይህ የተንኮል ምልክት በታየባቸው የምዕራባዊ ዞን ኣካባቢዎች ብቻ ሰርተን የምንተኛ ሳይሆን በራያ ኣንዳንድ ኣካባቢዎችም በልዩ ሁኔታ ደግሞ ራያ ኣላማጣ፣ ኦፍላ፣ በኮረም ከተማና ኣላማጣ ከተማ ጭምርም ሊሰራበት ይገባል። ለዚህ ደግሞ
በግልፅና በውስጣዊ ኣሰራር ሊተገበሩ የሚገቡ ኣንገብጋቢ መርሃ ግብሮች ኣሉ። እነዚህም፦
ሀ. በግልፅ ሊሰራባቸው የተገቡ መርሃ ግብሮች
የህወሓት ፓርቲ ገዢዎችና በትግራይ ክልል ብቻ የተመሰረቱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከመወነጃጀል ስራ ነፃ ሆነው በትግራይ የበላይነት ኣላማ ኣምነው የዚህ ክልልና ሃገር እድገት ለማረጋገጥ የኣቋምና የመተማመን የምናይበት ግዜ እየናፈቀን ነው። ይህ ኣሁን ያለንበት ግዜ ደግሞ ይሔን ጉዳይ ኣጥብቆ የሚፈልግበት ሁኔታ መሆኑ ማስተዋል ይጠይቃል። በኦሮሚያ ያሉ ተቃዋሚዎችና ገዢው ኦህዴድን ብናይ በሉኣላዊነትና የህዝብ የድህንነት መብትና ተጠቃሚነት የተዋሃዱና የተናበቡ ሆነው ይታያሉ።
በወረዳዎች ያለው የመልካም ኣስተዳደር እጦትና በሕብረተሰቡ መሰላቸትና ማጉረምረም ስለሚፈጥር ለእነዚህ እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎች የሚበቅሉበት በማዳበሪያ የተዘጋጀ ለም መሬት በራሳችን እየፈጠርንላቸው ስላለን በኣፋጣኝ የሚታረምበትና ስርኣትና መልክ የሚይዙበት ሁኔታ መፈጠር ኣለበት። ወደ ምዕራባዊው የትግራይ ዞን (ወልቃይትና ጠገዴ) የሚላኩት የተሾሙ የዞንና የወረዳ ኣመራሮች፣ የፍትህ ኣካላት በደጋማው የትግራይ ኣካባቢዎች ደካማ የስራ ኣፈፃፀም ያላቸውና ጥፋትም ያላቸው በቅጣት መልክ ወደ ኣካባቢው እንዲላኩ መደረጉ፤ መምህራን፣ የጤና ባላሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች ደግሞ ለስራቸው መጀምሪያ ልምድ
እንዲያገኙበት እንዲሆን ተደርጎ የተፈረደበት ኣካባቢ ነው። ይህ ደግሞ በኣካባቢው ልማትና መልካም ኣስተዳደር ትልቅ ኣሉታዊ ተፅእኖ ኣለው።
የመፍትሔ ሓሳብ፦ ያ ኣካባቢ በልማት ተጠቃሚ የሚሆንበትን በተጠቃሚነቱ በጎረቤቱ ከሚገኙት የኣማራ ክልል ወረዳዎች የተሻለ የልማት ተጠቃሚ ሆኖ በሚያይበት ግዜ ትግሬነቱ ኣጠናክሮ የሚቀጥልበትና ለሚመጡ የትግሬነቱ ጠላቶች በጣም ኣጠንክሮ የሚዋጋበት ሁኔታ ስለሚፈጥር በዚህ ጉዳይ በጣም ተጠናክሮ ቢሰራበት ዘላቂ መፍትሔ ያስገኛል። በተጨማሪ ከምዕራባዊው የትግራይ ዞን ውጭ ብንመለከት እንኳን በደርቅ የተጠቁ የኣማራ ክልል ወረዳዎች ዋግሀምራና ራያ ቆቦን በቂ የሰውና እንሰሳ ምግብና የመጠጥ ዉሃ ሲቀርብላቸው በኣንፃሩ ደግሞ በእነዚህ ኣከባቢ የሚገኙ የኣማራ ክልል ኣዋሳኝ የሆኑ የትግራይ ወረዳዎች እንደ ጣንቋ
ኣበርገሌ፤ ሰሓርቲ ሳምረና ራያ ለሰዉና እንሰሳ የሚያስፈልግ ምግብና የመጠጥ ውሃ ከጅምር በዘለለ የሚታይ ስራ ኣለ የሚያስብል ኣይደለም። ራያ ቆቦ ከከርሰ ምድር በሚገኝ ውሃ በመስኖ ሲለማ በኣንፃሩ ደግሞ ቀድሞ የተጀመረው የራያ መስኖ ስራ በትግራይ ስላልተሰራበት የራያ ትግራይ ህዝብ ለልማት ተጠቃሚነት ሲል ወደ ኣማራ ክልል ከሔድን እንደራያ ቆቦ እንለማለን የሚል መንፈስ ፈጥሮ ችግር እስከሚፈጠር ድረስ እንዲያድግ
ሰለማያስፈልግ በፍጥነት መፍትሔ ቢደርግለት ኣሁንም ጠቀሜታን ያስገኛል።
ሀ. በውስጣዊ ኣሰራር ሊተገበሩ የሚገባቸው መርሃ ግብሮች
1. ለእነዛ ከህግ ውጭ ኮሚቴ ኣቋቁመው በኣካባቢውና በውጭ (በኣሜሪክ ኣውሮፓና ሌሎች ኣግሮች)እየተንቀሳቀሱ ያሉትን ኮሚቴና ኣባላቶቹ ጉዟቸው የሚደናቀፍበትና በተጓዙበት ሁሉ እንቅፋትእንዲያጋጥማቸውና ተስፋ እንዲቆርጡ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል። ይሔም በዛ በሚንቀሳቀሱበት ቦታ ባሉትግሬዎችና የትግራይን ጣዕም በሚገባ የሚያውቁ ኣካላት በሚስጥር ሊሰራና ሊከናወን ይችላል። እነዚያ ኣባላቶቹ ጉዟቸው የሚያቋርጡበትና ከሕብረተሰቡ እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጫና እንዲያድርባቸው መስራት ያስፈልጋል። በዚህ የማይመለሱ ከሆነ ደግሞ ከሕብረተሰባቸውና ቤተሰቦቻቸው የሚለዩበት ስራዎች መስራት የግድ ይለናል። ለዚህ ሃሳብ የሚያንቀሳቅሱ ኣባላት፣ ኮሚቴውና ተባባሪዎቻቸው ከማህበራዊ ኣገልግሎት እንዲገለሉ መስራት፤ሆቴል ፣ መኪና ወዘተርፈ እንዲጠቀሙ በሚቀርቡበት ግዜ ለባለንብረቶቹና ኣግልግሎት ሰጪዎቹ የማንቂያ ሰራ በመስራት እነርሱ የሚፈልጉትን ኣገልግሎት እንዳያገኙ በማድረግ ባለንብረቶቹ ግዴታዎቻቸው እንዲወጡ መስራት ያስፈልጋል።
2. ይህ የትግራይ የቆላ ኣካባቢ ህዝብ (ምዕራባዊው ዞን)በደጋ ከሚኖረው የትግራይ ህዝብ ጋር ስነ-ልቦናዊና ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዲደለደል ማድረግ። የወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ወረዳዎች ካለፉት መንግስታት ጀምሮ እስከ ኣሁን ድረስ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቱና ማዕከሉ የጎንደር ከተማ ብቻ እንዲሆን ነው የተፈረደበት። የንግድ ሸቀጣ ሸቀጦች ከፋብሪካ ውጤቶች እስከ ኣትክልቶችና ፍራፍሬዎች የሚቀርብለት ከጎንደር ብቻ ነው። ለተጨማሪ የግል ትምህርት ልጆቹ የሚጓዙት ወደ ጎንደር ነው፤የሱዳን ሸቀጣ ሸቀጦች የሚገኝበት በመተማ በኩል ነው፤ በትግራይ ምዕራባዊው ዞን (በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ) እንደምንም ተጠጋግቶ ተጣቦ ኣርሶ ብር ያጠራቀመ ሰው ሲኖር ህንፃና የንግድ ቤቶች የሚሰራበትና የሚከትምበት ጎንደር ወዘተርፈ...ይህ በጣም ሓይለኛ የሆነ ስነ-ልቦናዊና ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ጫና ፈጥሮ ስለሚገኝ ይሔን ችግር ለመቀልበስ ደግሞ ደረሰኝ የሌላቸው ሸቀጣ ሸቀጦች ከጎንደር እንዳይመጡ የክልከላ ጫና ሰለባ እንዲሆን በማድረግ በተቃራኒው ከደጋማው የትግራይ ኣካባቢ ጋር ግንኙነት ለማጠናከር ደግሞ በሽሬና መቀሌ የሚገኙ ታላላቅ ነጋዴዎች በልዩ ሁኔት በማናገር በኣከፋፋዮች ደረጃ ከሁሉም ዓይነት የንግድ ዉጤቶችና ሸቀጣሸቀጦች ከጎንደር ከሚመጣው ንብረት ሁሉ በጣም በቀነሰ የዋጋ መጠን ቢያንስ ግን ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ሙሉ ብሙሉ የሚሸፈንበት መንገድ በኣጭር ግዜ ውስጥ መፈጠር ኣለበት። ከሽሬ ጀምሮ በሉግዲ በኩል የተዘረጋው ጥርጊያ (ሱዳንና ትግራይ የሚያገናኘው የጥርጊያ መስመር) በጣም ተጠናክሮ በፍጥነት እንዲሰራበትና ይህ የጥርጊያ መስመር እንዲጠናከር በጣም ጠንክሮ መስራትና ማገዝ፤ በዚህ ጉዳይ ከሱዳን ጋር በጥልቅትና በፍጥነት መወያየት ያስፈልጋል።
የትግራይ ኪነ-ጥበብ በተለይ የትግርኛ ዘፈኖች ብናያቸው በሁሉም ዘፈኖቹ ሲጠሩ የምንሰማቸው የኣካባቢ ስሞች ትግራይ ማለት ከሽሬ የሚመለስ እንደሆነ የሚሰብኩ ናቸው። ይህን ችግር ከመሰረቱ በማረም ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ሁመራ ያካተተ እንዲሆን የትግራይ ጥበበኞች እንዲያስቡበት ማድረግ፤ ምክንያቱም በኣማርኛ ቋንቋ የሚዘፈኑ የጎንደር ኣካባቢ ስም የሚያነሱ ዘፈኖች ሁሉ ብንመለከት ኣሁንም ያልተዋቸው በሽታ የእነዚህ ኣካባቢ (ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሰሜን፣ኣርማጭሆ፣ጠለምትና ሁመራ) ስም ሳይጠሩ ኣያልፉም። ስለሆነም የጥበብ ድርሻ በሰው ልጅ ስነ-ልቦና ከፍተኛ ተፅእኖ ስላለው የትግራይ ጥበበኞች ልንሰራበት ይገባል። የቆላው የትግራይ ተወላጅ (ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሁመራ፣ ቃብቲያና ጠለምት) ከጎንደር ታሪክ በላይ በኣክሱምና ይሓ ታሪክ ኩራት እንዲሰማዉና የእኔነት ስሜት እንዲያድርበት ማድረግ የግድ ያስፈልጋል። ከኣጤ ቴድሮስ ታሪክ በላይ የኢትዮጵያን ዳርድንበርን ለማስከበር ላይ እና ታች እያለ ሳለ የሞተውን የኣጤ ዮሃንስ ኣራተኛ ጀግንነት ኣውቆ እንዲኮራበትና እንዲመካበት ቢደረግ የትምክህተኞቹ የኣማራዎቹ ተግባር ማለትም ከድሮ ጀምሮ በተዋረድ የመጣውን ክፋታቸውና ዉሸታቸው እንዲሁም የትግራዋይን ስም የማጥፋትና በወሬ በማስተጋባት ብልግና እንደሰሩ በማስተማር በተቃራኒው ደግሞ የትግራይና ትግራዎትን የበላይነትንና ብሔርተኝነትን ከፍ በማድረግ በውስጣዊ ስብከት እንዲያስተጋባ በማድረግ ጫና መፍጠር።
3. የሐይማኖት ኣባቶች ግዴታዎች፦
በኣካባቢው ኣብዛኛው የኦርቶዶክስ ሐይማኖት እምነት ተከታይና የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ በመሆኑ በኣብያተ-ክርስቲያናት ላይ የሚደረጉት ስብከቶችና ኣገልግሎቶች ከኣማርኛ ሙሉ በሙሉ ነፃ እንዲሆኑ በማድረግ በትግርኛ እንዲገለገሉ ማድረግ። በኣከባቢው ወደ ሚገኙ ኣብያተ-ክርስቲያናት የሚመደቡ ገበዝ፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት ከኣካባቢ ሰዎች እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ ሙሉ በሙሉ ትግርኛ ብቻ የሚናገሩ ኣገልጋዮች ከሁሉም የደጋው የትግራይ ኣካበቢ የሚመደቡበት ሁኔታ በማመቻቸት የመስበኪያ ቋንቋ ትግርኛ እንዲቆጣጠረው ማድረግ። ይህም ማለት ያ ኣሁን ያለው የኣካባቢው የኣብያተ-ክርስቲያናት ኣገልግሎት የኣማርኛ ቋንቋ የበላይነት የሚያራምዱ የጎንደሬዎችና የጎጃሞች ቋንቋ ለትግርኛ ቋንቋ የሚቆጣጠረው ስለሆነ ነው።
4. የኣካባቢው ተወላጅ የሆኑ ተሰሚነት ያላቸው የኣገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት መሪዎችና ሃብታሞች ትግሬነታቸው እንዲኮሩበትና ለእነዛ በመሓል ስሜት ያሉ ሰዎች ሰብከው የሚያመጡበት ሁኔታዎች ለመፍጠር መነጋገርና መግባባት በመፍጠር እንዲሰሩበት ማድረግና በልዩ እንክብካቤ መያዝ ያስፈልጋል።
5. የኣካባቢው ኗሪ ተወላጆች በመንግስት ስራዎችና በግል ስራዎች በሁሉም የትግራይ ደጋማው ኣካባቢ ከሚኖሩብት የተሻለ ስራ እንዲሰሩ ማድረግና ከትግራይ ነጋዴዎች ጋር ጥብቅ ሁኔታዎችና ግንኙነት እንዲኖር መፍጠር። በተቃራኒው ደግሞ ወደ ትግራይ ምዕራባዊው ዞን የደጋማው የትግራይ ህዝብ በብዛት በማምጣት ቋሚ ኑሮ የሚኖርበትና የሚመራበት ሁኔታዎች በመፍጠር ይህ መርሃ ግብር በፍጥነት እውን እንዲሆን ማድረግ ኣስፈላጊ ነው።
6. ኣዳዲስ የሰፈራ ማዕከሎችን በማቋቋም በሸራሮና ሁመራ የጥርጊያ መስመር ፈቃደኛ የወልቃይትና የጠገዴ ተወላጆች በዛ ኣድርገን ከሌላ ኣካባቢዎች ኣደባልቆ በሰፈራ ማዕከሎች ማስፈር። በኣማራ ክልል ድንበር የሚገኙ ኣዋሳኝ የወልቃይትና የጠገዴ ቀበሌዎች ላይ ከትግራይ በሚመጡ ሰፋሪዎች በቋሚነት እንዲሰፍሩና በእርሻና ንግድ በጣም ፈጣንና ጠንካራ እንዲሆኑ በማድረግ የተለያዩ የብድር ኣገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ እንዲሁም ግብር እንዳይከፍሉ በማድረግ በቋሚነት የሚኖሩበት ሁኔታ ማመቻቸት።
7. በባላባት የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆችና ለስራ ከደጋው የትግራይ ኣካባቢበሔዱትና በሚሔዱት የትግራይ ተወላጆች መካከል በትዳር በሰፊው እንዲገናኙ በማድረግ የትግራይ ልጆች ኣንድነት እንዲጠነክር መስራት ያስፈልጋል። በመጨረሻ እነዚህ የመሳሰሉትን የሚነሱ ጥያቄዎች የሚከታተል ውስጣዊና ሚስጥራዊ ኮሚቴ በማቋቋም መፍትሔዎችን ያፈላልጋል፤ በትምክህተኛ የኣማራ ሓይል በኩል የሚደረጉ ዉስጣዊና ዉጫዊ እንቅስቃሴዎች በትኩረት መከታተል ያስፈልጋል።
No comments:
Post a Comment