Friday, August 5, 2016

ዛሬ ደግሞ ምን እንደሚሉ እንሰማለን (በሃብታሙ ዙሪያ) -ግርማ ካሳ


ሃብታሙ አያሌው ወደ ዉጭ ሄዶ እንዲታከም ጠበቃ አማሃ ፍርድ ቤቱን እያለቀሱ ጠየቁ። ፍርድ ቤቱ፡
1. ለአንድ ወር ቀጠሮ ሰጠ፤ ለሃብታሙ ስቃይና ሕመም ደንታ ሳይኖረው (በሃብታሙ ሕመም ጉዳይ ቀጠሮ 1)
2.
ሃብታሙ ኮማ ዉስጥ ገባ፣ ሕመሙ በጣም ጸንቶበት። ጠበቃ አመሃ ድጋሚ ወደ ፍርድ ቤት ሄዱ። ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመስማት ቀጠሮ ሰጠ (ቀጠሮ 2)
3.
በቀጠሮው ቀን ዳኛው ከሃኪም ወረቀት ይጻፍ ብለው ሌላ ቀጠሮ ሰጡ። (ቀጠሮ 3)
4.
የሃኪም ደብዳቤ ለፍርድ ቤቱ ቀረበ የሕክምና ቦርዱ ካልሆነ በሚል ሌላ ቀጠሮ ተሰጠ። (ቀጠሮ 4)
5.
የሕክምና ቦርድ ዉጭ ሄዶ መታከም አለበት ብሎ ደብዳቤ ጻፈ። ፍርድ ቤቱ ከአቃቢ ሕግ በቃል አስተያየቱን ያቅርብ ተብሎ ቀጠሮ ሰጠ። ( ቀጠሮ 5)
6.
አቃቢ ሕግ በቃል አስተያየቱን ሊሰጥ ሲዘጋጅ ፍርድ ቤቱ "አይደለም በጽሁፍ ይቅረብለን" በሚል ሌላ ቀጠሮ ተሰጠ። (ቀጠሮ 6)
7.
አቃቢ ሕግ በጽሁፍ ምንም አስተያየት እንደሌለው ገለጸ። ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ከመወሰን ይልቅ ከጠበቃ ደግሞ መስማት አለብን" በሚል ጠበቃ አመሃ በደብዳቤ አስተያየታቸውን እንዲያቀርቡ ሌላ ቀጠሮ ተቀጠረ። (ቀጠሮ 7)
8.
ጠበቃ አመሃ የተጠየቁት አቀረቡ፣ እንደገና ሌላ ቀጠሮ ለዛሬ ሐምሌ 29 ቀን እለተ አርብ ተቀጠረ። በሃብታሚ ሕክምና ዙሪያ ስምንተኛ ቀጠሮ መሆኑ ነው።
እንግዲህ ሕግ ሕግ የሚሉ ፍትህ ፍትህ የሚሉን ይሄንን ነው !!!! ወያኔዎቹ .....የተጨማለቀዉን የፍርድ አሰራር።
በዚህ መሃል አቶ ሃብታሙ አሁን በአልጋ ላይ ነው። የሚሰጠው መርፌ እጆቹን ስላቆሰሉት በእግሩ ሆኗል የሚወጋው መድሃኒቶች ለመዉሰድ። ይሄ ሁሉ ሲሆን ግን ወያኔዎች ለፍርድ ቤት ቀጥተኛ መመሪያ እየሰጡ ይሄንን ታላቅ ጀግና በበቀል እያሰቃዩት ነው። መጀመሪያዉኑ ለሕመም የዳረጉት እነርሱ ናቸው። ቶርቸር አደርገዉት። አሁን ደግሞ ምናልባት የተነሱ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ካላስደነገጣቸው በቀር ሃብታሙ በሕመሙ ታሞ እንዲሞት የወሰኑ ነው የሚመስለኝ።
ሰዎቹ በጣም ቂመኛ ናቸው።፡ኢትዮጵያን የሚወድ ሰው፣ ለኢትዮጵያ የቆመን ሰው ይጠላሉ። ለሕዝብ መብት የሚሟገት ሰው አይወድም። እነርሱ ሃብታሙን እንደ ወንጀለኛ እያዩት እያሰቃዩት ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄ ወጣት እየከፈለ ያለው መስዋእትነት ያወቃል። ለዚህም ነው በየአደባባዩ የዚህ ወጣት ፎቶ የሚያወለበልበው። ሃብታሙ አይሞትም። ሃብታሙ ይደናል። ሃብታሙን እና የሃብታሙ ቤተሰቦች ክለሕወሃት መመሪያ እየተቀበሉ ሲያጉላሉ የነበሩ ዳኛ ተብዬዎች፣ አቃቢ ሕጎች ሁሉም ማን እንደሆኑ ይታወቃል። "ታዝዤ፣ እንጀራ ሆኖብኝ ነው .." እያሉ ሰበብ መስጠት አይሰራም።

እንግዲህ ዛሬ ደግሞ ምን እንደሚሉ እንሰማለን

No comments: