Saturday, June 11, 2016

ትግሉ ወደ ሜዳ ይዉረድ

የሕግ ባለሞያ ነው፣ ጠበቃ። አገሩን እና ህዝቡን የሚወድ ኢትዮጵያዊ። በሞያው ሕሊናዉን ሽጦ፣ በሕዝብ ላይ የግፍ ቀንበር እየጫነ ያለው የኢሕአዴግ አገዛዝ አካልና አገልጋይ ሆኖ፣ ያንንም በማድረጉ የስርዓቱ ተጠቃሚ ሆኖ መኖር ይችል ነበር። ግን ሕሊናው አልፈቀደለትም። ወይንም ራስ ወዳድ ሆኖ፣እኔ ላይ እስካልመጡ ድረስ ምን አገባኝብሎ፣ በወገኖቹ ላይ የሚደርሰዉን ግፍ እንዳላየ አይቶ ዝምታን መርጦ መኖር ይችል ነበር።
ግን አላደረገዉም። ለስብእና፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነት መቆምን ፈለገ። አገርና ህዝብን ማገልገልን መረጠ። ድምጻቸው ለታፈኑ፣ ለታሰሩ፣ ለተገፉ፣ ቀንበር ለበዛባቸው ድምጽ መሆን ፈለገ።

ይህ ተግባሩ በግፈኞች አልተወደደለትም። አስፈራሩት። ደበደቡት። አርፎ እንዲቀመጥ ጫና አደረጉበት። ግን እስሩ አልበገረውም። በማንኛውም ጊዜ የባሰው ነገር ሊፈጽሙበት እንደሚችሉ ተረዳ። ቢሆንም ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት ተዘጋጀ። አልፈራም። ማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለሃገሬ እና ለነጻነት ነው። በአካል ብታሰርም ሕሊናዬ አይታሰረም። ከገደሉኝም ትግሌን አደራ ብሎ መልእክት አስተላለፈ።
ደም ማፈሰስ የለመዱ ግፈኞች ግን፣ ለስብእና ቅንጣት ያህል ደንታ የሌላቸው ግፈኞች ስለሆኑ በድጋሚ በትራቸውን አነሱበት። በግፍ በጭካኔ ገደሉት። ሳሙኤል አወቀ፣ ነዋሪነቱ በጎጃም የሆነ ጠንካራ የሰማያዊ አመራር አባል።

የሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ባደረገው ስብስበ ሳሙኤል አወቀን እኔ ሌሎች ለትግሉ ዋጋ የከፈሉትን ዘክሯል። በጽ/ቤቱ። ዶር ዳኛቸው አሰፋ እና አቶ ግርማ በቀለ ትምህርት ሰጪ ገለጻዎችን አደርገዋል።

ሳሙኤል አወቀን እኔ ሌሎችን በሰማያዊ ፓርቲ /ጽቤት ደርጅቶች በዚህ መልኩ ማስታወሳቸው ጥሩ ከመሆኑ በተጨማሪ አስፈላጊም ነው። የታሰሩ እስረኞችን እና ዋጋ የከፈሉ ወገኖችን የሚረሳና የማያስታወስ ደርጅት ትግሉን ወደፊት ሊያራምድ አይችልም።

ሆኖም የሰማያዊ ፓርቲ ትግሉ በአዲስ አበባ በካሳንሺስ /ቤት ዉስጥ ብቻ ሳይወሰን፣ መግለጫዎችን በማውጣት ብቻ ሳይወሰን፣ ወደ ሜዳ ወደ ህዝቡ የሚወርድበትን ስትራቴጂ በመርዘጋት ቢንቀሳቀስ ግን የበለጠ ጥሩ ይሆናል። ትግሉ ያለው ህዝቡ ጋር ነው። ሌሎቻችን ሰማያዊና ሌሎች አገር ቤት ያሉ ደርጅት ዓባልት በራሳቸው ብቻ ለዉጥ ሊያመጡ እንደማይችሉ ተገንዝበን አገር ቤት ያለን የነዚህ ደርጅቶች አባላት በመሆን፣ ከአገር ዉጭ ያለን ደግሞ ዕነዚህ ደርጅቶች በመደገፍ፣ ድርጅታዊ ብቃታቸው እንዲያጠናክሩ ማድረግ መቻል አለብን።

ይሄን ስል ሰማያዊም ሆነ ሌሎች ችግሮ የለባቸውም ማለት አይደለም። ግን ችግር አለባቸው ብለን ብሶት ከምናሰማ ከችግሮቻቸው እንዲወጡ መርዳት ይሻላል። ወደቁ ብለን የለበጠም ረግጠናቸው ከምንሄድ እጆቻችንን ዘርግተንን ብናነሳቸው ይሻላል።


No comments: