Monday, June 13, 2016

ሕወሃት ከኤርትራ ጋር ጦርነት መግጠም ለምን አስፈለገው?


ጉዳዩ የትኩረት አቅጣጫን ለማስቀየር ስለመሆኑ ሌላም ማረጋገጫ አለ። በፆረና ግንባር ስለተቀሰቀሰው ጦርነት ከመደበኞቹ የህወሃት ሚድያዎች ቀድመው ዜናውን እንዲያሰራጩ የተነገራቸው ዳዊት ከበደ (አውራምባ ታይምስ) እና ዳንኤል ብርሃኔ (ሆርን አፌር) ሁለቱም የወያኔን ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት የሚታወቁ የህወሃት አፈቀላጤ (mouthpiece) ናቸው። ምናልባትም ህወሃት ተኩስ ከመጀመሩ በፊት ይሆናል ዜናውን እንዲያሰራጩ የተነገራቸው።
-----------------------
(ECADF)—
የኤርትራ ኢንፎርማሽን ሚኒስቴር ባወጣው አጭር መግለጫ "ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ሕወሃት) እሁድ ሰኔ 5-2008 በፆረና ግንባር አላማና ምክንያቱ ያልታወቀ ጥቃት ሰንዝሯል፣ የኤርትራ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መግለጫ ይሰጣል" ብሏል።
ሕወሃት 1983 . ኢትዮጵያ ከመቆጣጠሩ በፊትና ከዚያም በኋላ ለሰባት ዓመታት ከኤርትራው ሕዝባዊ ግንባር (ሻብያ) ጋር የጠበቀ ግንኙነት የነበረው ሲሆን 1990 . በድንገት ለስልጣን ካበቃው ሕዝባዊ ግንባር (ሻብያ) ጋር ጦርነት ውስጥ ገብቷል። በአንድ ወቅት ሟች የሕወሃት ቁንጮ መለስ ዜናዊ ከኤርትራ ጋር ስለነበራቸው ግንኙነት ሲገልጽ "ግንኙነታችን ልክ እንደ መርፌና ክር ነው..." በማለት ማስረዳቱ ይታወሳል።
ይሁንና 1989 . በድንገት መልኩን የቀየረው ግንኙነታቸው ወደ ጦርነት አምርቶ 70,000 እስከ 100,000 ለሚገመት የሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል። በወቅቱ ሕወሃት ያለምንም ጡረታ የበተናቸውን የቀድሞ መከላከያ ሰራዊት አባላት በአዋጅ ጠርቶ ጦሩን ለማጠናከር ሞክሯል፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችንም የለብ ለብ ስልጠና ሰጥቶ ለጦርነቱ አሰልፏቸዋል። ሁለት ዓመት የፈጀው ጦርነት ሲያበቃ በአብዛኛው ህይወታቸውን ያጡት ነባሮቹ የሕወሃት ታጋዮች ሳይሆኑ የለብ ለብ ስልጠና ተሰጥቷቸው ለጦርነት የተማገዱት የኢትዮጵያ ወጣቶች ነበሩ። ጦርነቱ ከቆመ በኋላ ከሞት የተረፉት ወጣቶች 2000 ብር እየተሰጣቸው እንዲበተኑ ተደርጓል።
ሕወሃት ከኤርትራ ጋር ጦርነት መግጠም ለምን አስፈለገው?
1997 . እና ከዚያ በኋላ የሆነውን ማስታወስ ተገቢ ነው። ሕወሃት 1997 በተካሄደው ምርጫ ክፉኛ በተሸነፈ ማግስት የድምጽ ኮሮጆዎችን ገልብጦ፣ የሚገድለውን ገድሎ፣ የሚያስረውን አስሮ ሲያበቃ የጋመውን የህዝብ ተቃውሞ ለማብረድና የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር ሶማሊያ ውስጥ ዘው ብሎ ገብቶ ዛሬም ድረስ ሊወጣው ያልቻለበት አዘቅጥ ውስጥ ይገኛል።
እናም ሕወሃት አሁንም የህዝቡን የትኩረት አቅጣጫ ማስቀየር ግድ ሆኖበታል። በኦሮሚያ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋብ ያለ ቢመስልም እያሰለሰ ቀጥሏል፣ የወልቃይት ህዝብ ለዓመታት የተጫነበትን የሃሰት (የትግሬ) ማንነት አልቀበልም ብሎ አምጿል፣ በጎንደር ዳባት ህዝቡ የተለመደ የወያኔን ዘረፋ እምቢኝ ብሎ ከወያኔዎቹ ጋር ተፋጦ ይገኛል፣ አርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ የህዝብ ተቀባይነት ባለው መሪው በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እየተመራ በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ብቻም ሳይሆን በደቡብ ጋሞጎፋ (አርባምንጭ) ድረስ እየዘለቀ ወያኔን ፋታ አሳጥቶታል፣ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ለአርበኞቹ ያለውን አጋርነት በማሳየት ላይ ነው።
እነዚህ ምክንያቶች ህወሃት የህዝቡን የትኩረት አቅጣጫ እንዲያስቀይር ግድ ይሉታል።
ጉዳዩ የትኩረት አቅጣጫን ለማስቀየር ስለመሆኑ ሌላም ማረጋገጫ አለ። በፆረና ግንባር ስለተቀሰቀሰው ጦርነት ከመደበኞቹ የህወሃት ሚድያዎች ቀድመው ዜናውን እንዲያሰራጩ የተነገራቸው ዳዊት ከበደ (አውራምባ ታይምስ) እና ዳንኤል ብርሃኔ (ሆርን አፌር) ሁለቱም የወያኔን ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት የሚታወቁ የህወሃት አፈቀላጤ (mouthpiece) ናቸው። ምናልባትም ህወሃት ተኩስ ከመጀመሩ በፊት ይሆናል ዜናውን እንዲያሰራጩ የተነገራቸው።


ECADF Ethiopian News

No comments: