Wednesday, June 15, 2016

በሶማሌና ኦሮሚያ ክልል ኩንቢ ወረዳ ድንበር ላይ በተቀሰቀሰ ግጭት አንድ ፖሊስን ጨምሮ 10 ሰዎች ተገደሉ

ሰኔ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :-በክልሎቹ ድንበር አዋሳኝ ላይ በምትገኘው ኩንቢ ወረዳ በሁለቱ ብሔረሰቦች መሃከል በተቀሰቀሰው የድንበር ግጭት ሳቢያ ከሞቱት መካከል ዘጠኙ ሰላማዊ ዜጎች ሲሆኑ አንድኛው የልዩ ጦር አባል ናቸው። በትናንትናው እለት ሰኔ 7 ቀን 2008 .. የተፈጸመውን ዘግናኝ እልቂት በዋነኛነት ትእዛዝ በመስጠት ሲመሩ የነበሩት የሶማሊያ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሃመድ ኡመር መሆናቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። ይህን ተከትሎ በፕሬዝዳንቱ የሚመራው ልዩ ጦር በወሰደው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ምክንያት ዘጠኝ የኦሮሞ ብሔርተወላጆች መገደላቸውና በአጸፋውም አንድ የልዩ ጦር ታጣቂ መገደሉ ታውቋል። የፌደራል ፓሊስ አባላት ወደ ቦታው ሄደው ሕዝቡን ካረጋጉ በኋላ ለልዩ ኃይሉ አስረክበውመውጣታቸው ተከትሎ ግጭቱ መቀስቀሱ ሲታይ ሆንተብሎ በፌደራል ፖሊስ የተቀነባበረ ሴራ እንደሆነ ያመላክታል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል።በተጨማሪም በሶማሌና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ከነገሌ ቦረና 30 .. እርቀት ላይ በሶማሌ መርሃን ጎሳ አባላትና በቦረናዎች መሃከል ከፍተኛ ፍጥጫ ተፈጥሮ የግጭት ስጋት አንዣቧል። በአሁኑ ወቅት ሁለቱም ወገኖች መሳሪያቸውን አንግበው ምሽግ ይዘው በደፈጣ ላይ የሚገኙ በመሆናቸው የአካባቢውም ነዋሪዎች ከደኅንነት ስጋት ጋር በተያየዘ በስጋትና ጭንቀት ውስጥ መውደቃቸውን ምንጮቻችን አክለው ዘግበዋል።

No comments: