Tuesday, June 14, 2016

ሁለት ሙት ዘጠና ሚሊየን ቁስለኛ!!

(አሌክስ አብርሃም)
አንዳንዴ ጀብዱ የሚመስለን ነገር የለየለት ደንቆሮነት የሚሆንበት ጊዜ አለ ! ይታያችሁ ይህ ሰው የኛው ጉድ ነው .... የስርዓቱ አፈቀላጤ !! እንዲህ በኩራት አጠገቡ ቁጭ ያለው የአንድ አልሸባብ ተዋጊ አስከሬን ነው ... በግራ የተገደለ የአልሸባብ ተዋጊ ሬሳ በቀኝ የኛው "ጋዜጠኛ" በሱ ቤት ትልቅ ነገር መዘገቡ ነው ...አሸነፍን ድል አደረግን ለማለት !!በድሮ ነገስታት ታሪክ እንኳን የጠላት አስክሬን ይከበራል ..ምክንያቱም አስከሬን የፖለቲካ አቋም የለውም ! አስከሬን አጠገብ ተቀምጦ የለት እንጀራውንና የፖለቲካ ትርፍ የሚለቃቅም ጥንብ አንሳ ብች ነው !!
የሚያሳዝነው ግን የኛም ወታደሮች በሰው አገር እንዲሁ በረሃ ላይ ወድቀው መቅረታቸውን ከዚህ ሰበአዊ ክብሩ ከጎኑ እንደወደቀው ሬሳ የሞተበት ጋዜጠኛ በላይ ማን ያውቃል? (ያው አለም የዘገበው ጉዳይ ነው) ለማንኛውም እኔ እዚህ ፎቶ ላይ ሁለት ሬሳና ሞታቸው ለህዝባቸው በክብር ይፋ ባለመደረጉ ልቡ ያዘነ ዘጠና ሚሊየን ህዝብ ነው ...ሁለት ሙት ዘጠና ሚሊየን ቁስለኛ!! ኢትዮጲያዊያን ክብራችን ጀግንነታችን ተፈጥሯዊ ሰብዓዊነታችን ነው !!


No comments: