Tuesday, June 28, 2016

የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ ሐብታሙ አያሌው በጠና ታምሞ ኮማ ውስጥ ገብቷል።

ሃብታሙ አያሌው፣ አገሩን እና ህዝቡን በማገልገሉና በመዉደዱ "ሽብርተኛ" ብለዉት በማእካላዊ ባደረሱበት ከፍተኛ ስቃይ፣ በሽታዎችን ሸምቶ መዉጣቱ የሚታወስ ነው። ሁለቱም ኩላሊቶቹ ላይ ችግር የተፈጠረ ሲሆን ከፍተኛ ደረጃ በደረሰ ሄሞራይድም እየተሰቃየ ነው።
ሃኪሞች ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰርጀሪዉን ማድረግ በጣም አሰቸጋሪ እንደሆነ ገልጸው ዉጭ ሄዶ እንዲታከም ቢጠይቁም፣ መጀመሪያዉኑ በወህኖ ሊሰቃዩት ሕመም እንዲሸምት ያደረጉ ወያኔዎች፣ ወጥቶ እንዳይታከም በመከልከላቸው ሕመሙ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ወንድማችን ለዚህ ተዳርጓል። የአቶ ሃብታሙ አያሌው ጠበቃ በልቅሶ ዳኛው ተብዬው ተማጽኖ ቢያቀርብም ዳኛ ከሕወሃት በተሰጠው ትእዛዝ ሃብታሙ ወጥቶ እንዲታከም ለመፍቀድ ፍቃደኛ አይደለም።
እግዚአብሄር እንዲያስበው፣ እንዲፈዉስ እጸልያለሁ። ሁላችንም በያለንበት እንጸልይ። ወንድማችን አንድ ነገር ቢሆን ወያኔዎች ሽጉጥ አውጥተው ግንባሩ ላይ ተኩሰው እንደገደሉት ነው የምቆጠረው። ዳኛውን ነፈሰ ገዳይ እንደሆነ ነው የምንቆጠረው።
እነርሱ ጀነራል ቼክ አፕ ለማድረግ አሜሪካ እየመጡ፣ ከህዝቡ በዘረፉት ገንዘብ ሲታከሙ፣ ሌሎች በከፈተኛ ሕመም ላይ እያሉም፣ እንዳይታከሙ ማገድ ከሰይጣንነት የባሰ ጭካኔ ነው።
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በደረሰኝ መረጃ ሃብታሙ አያሌው ኮማ ዉስጥ ነው። ይተነፍሳ፣ ደም ግፊቱን ደህና ነው። ግን አይሰማ፣ አያይም፣ አይናገርም። ዶክተሮቹ ችግሩ ምን እንደሆነ እስከአሁን አላወቁም።


No comments: