Saturday, June 11, 2016

መረጃ… ማስጠንቀቂያ ለዳባት አካባቢ ህዝብ

Map of Dabat town Ethiopia
በልኡል አለም
በ 2007 ዓ/ም የተደረገ የህዝብ ቆጠራዎች ሊስት እንደሚያመለክተዉ 145.509 ህዝብ በዳባት ይኖራል ከ1994 ዓ/ም ጀምሮ በ22% ህዝብ መጨመሩን መረጃዉ የሚያመለክት ሲሆን 73,852 ወንዶች 71,657 ሴቶች በዳባት ወረዳ የሚኖራሉ፣ ዳባት በ 1.187.93 ስኳር ኪ/ሜ ስፋት ላይ ትገኛለች በዳባት ወረዳ ዉስጥ  97.7 % ያህሉ ህዝብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ነው 2.4% ደግሞ እስልምና እምነት ተክለታዮች ናቸዉ።
የዳባት ህዝብን ለየት የሚያደርገዉ ነገር ቢኖር አትንኩኝ ባይና ከነኩትም የማይመለስ በመሆኑ ነው፡ ዳባት በሰሞኑ ከትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን ጋር በገጠመዉ አለመግባባት ምክንያት በብዛት ዱር ቤቴ ብሏል!
የሰሜኑ ጎንደር አይበገሬ ወረዳ ህዝብ ዳባት በደቡብ በኩል ወገራ የሚያዋስነዉ ሲሆን በምእራብ ታች አርማጭሆ እንዲሁም በሰሜን ምእራብ ጠገዴ እና በሰሜን ምስራቅ ደባርቅን ይዋህዳል ዳባት ክተት ካለበት ወቅት አንስቶ ለወያኔ ልዩ ኃይልና ለመከላከያ ሰራዊት የማይቀመስ በመሆን እንቅልፍ ነስቷል!
በመሆኑም ወያኔ የዳባትን ህዝብ ዙሪያዉን ለመክበብና ለመዉረር ከመከላከያ ሰራዊት በተላለፈ ትእዛዝ መሰረት እየተንቀሳቀሰ ነው በጠገዴና በደባርቅ እንዲሁም ከራስ ዳሽን ተራራ አካባቢ በሶስት አቅጣጫ ዳባትን ለማንበርከክ የወያኔ ሰራዊት ዝግጅቱን በማጠናቀቅ የአሰሳ መመሪያ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
በመሆኑም በማላዉ ዳባትና በዳባት ዙሪያ የሚገኙ የዉስጥ አርበኞች ወረራዉን ለመመከት በመከላከያ ሰራዊቱ ዉስጥ የሚቻላቸዉን እንደሚያደርጉ እያስጠነቀቁ ህዝቡ የበኩሉን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አደራቸዉን አስተላልፈዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

No comments: