Thursday, June 9, 2016

የኢትዮጵያ መንግስት “ተቃዋሚዎች እግር ሲያወጡ መቁረጥ” የሚል ስትራቴጂ እንደሚከተል ዶ/ር መረራ ተናገሩ

የኢትዮጵያ መንግስት ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ የመቻቻል ፖለቲካ የሚከተል በማስመሰል በአገር ውስጥ ግን ተቃዋሚዎችን መፈናፈኛ አሳጥቶ እንደሚገኝ / መረራ ገለጹ።
የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ወህኒ ቤት መውረዳቸውንና ቢሮዎቻቸው ባዶ መሆናቸውን / መረራ ጉዲና አሜሪካ አገር ለሚገኘው ኤን አር ለተባለ የሬዲዮ ጣቢያ ተናግረዋል።
በቁም እስር ከሚገኙት የፓርቲው ጸሃፊ በተጨማሪ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ምክትል ሊቀመንበር፣ ረዳት ጸሃፊ፣ እና ስድስቱ የፓርቲ ሊግ አባላት ሁሉም በመታሰራቸው የፓርቲው ቢሮ ባዶ እንደቀረ / መረራ አክለው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ መንግስትስ የሚነቅፉ ሰዎች መጨረሻቸው ወህኒ ቤት ቢሆንም፣ የኢህአዴግ መንግስት እርሳቸውን ለምን እንዳላሰረ ለቀረበላቸው ጥያቄ / መረራ ሲመልሱ፣ ጉዳዩ 21ኛው ክፍለ ዘመን ቁማር ነው ብለዋል። ኢዲሞክራሲያዊ የሆኑ መንግስታት እየተራቀቁ መምጣታቸውን ገልጸው፣ ተቃዋሚዎችን ሙሉ በሙሉ ከማጥፋት ይልቅ የመቻቻል ፖለቲካና የብዙህን ፓርቲ ያለ በማስመሰል እንደሚተውኑ ገልጸዋል።
በቀድሞ መሪ መለስ ዜናዊ 1997 ምርጫ ማግስት የታቀደው እቅድተቃዋሚዎች እግር እስከሚያወጡ መጠበቅና ከዚያም መቁረጥእንደሆነ ያስታወሱት / መረራ፣ እሳቸውም የዚህ እቅድ ምሳሌ እንደሆኑና ሌሎቹ የፓርቲ አባላት በመታሰራቸው የፓርቲያቸው እግር ተቆርጦ እሳቸው ግን ያለ እግር እየተንሳፈፉ እንደሆነና እሳቸው ብቻቸውን ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ለሬዲዮ ጣቢያው በምሳሌ አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከዲሞክራሲ ጎዳና ወጥቶ ወደአልታወቀ አቅጣጫ ጎዳና እየነጎደ ነው ሲሉ / መረራ ለኤን አር (NPR) ገልጸዋል። ሁሉንም ሰው ማሰር እንደማይቻል የተናገሩት / መረራ፣ መሪዎች በታሰሩ ቁጥር መሪ የሌላቸው አመጾች በየቦታው እያቆጠቆጡ እንደሆነ ገልጸዋል። ለዚህም ባለፈው ህዳር በኦሮሚያ የተነሳውን አመጽ በአብይነት ጠቅሰዋል።

ኢሳት

No comments: