Monday, June 27, 2016

እነ አቶ በቀለ ገርባ ጨለማ ቤት ታስረው ተፅዕኖ እየተደረገባቸው መሆኑ ተገለጸ

በፌዴራሉ ከፍተኛ /ቤት 19 ወንጀል ችሎት ሰኞ ዕለት የቀረቡት እነ አቶ በቀለ ገርባ አሁንም በጨለማ ቤት እንደሚገኙና ተፅዕኖች እንደቀጠሉባቸው ተገለጸ። ፍርድ ቤቱም ክሱ በሽብር ያስከስሳል አያስከስስም በሚል ውሳኔ ለመስጠት ከሃምሌ 25 ቀጠሮ በመስጠት መነሳቱም ታውቋል።
በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰን ከመንፈቅ በላይ የቀጠለውን ተቃውሞ ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት የኦፌኮ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች አመራሮች ከግንቦት 26 2008 ጀምሮ በጨለማ ቤት ውስጥ መቀጠላቸውን ለችሎቱ የገለጹት አቶ ደረጀ ፊጣ ገለታ ሲሆኑ፣ እርሳቸውን ጨምሮ አራቱ ተከሳሾች ያሉበት ጨለማ ቤት መታጠቢያ/መጸዳጃ ቤቱ ውስጥ እንደሚገኝና ክፍት መሆኑን ገልጸዋል።
ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ የሚፈቀደው ከአምስት እስከ 15 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ መሆኑን በማብራራት በጨለማ ቤት በሚገኙት አራት እስረኞች የሚደረገውን ጫና ዘርግተዋል።
የተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት አቶ አምሃ መኮንን በበኩላቸው የእስር ቤቱ አስተዳደር አደረሰ ያሉትን ጫና ዘርዝረዋል።
በተለይ ደንበኛው አቶ በቀለ ገርባ ተገቢውን መድሃኒት እንዳያገኙ መደረጉን፣ ተከሳሾችን አነጋግረው ሲወጡ ማስታወሻቸው በእስር ቤቱ ሃላፊዎች እንደሚወሰድባቸው ለችሎቱ አስረድተዋል። /ቤቱም የእስር ቤቱ ሃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ለሰኔ 27 2008 ቀጠሮ ሰጥቷል።
ኢሳት 

No comments: