Wednesday, June 15, 2016

በመፈንቅለ መንግስት በተከሰሱት በጄነራል ተፈራ ማሞና በጀነራል አሳምነው ጽጌ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸው ሆስፒታል ገቡ

ሰኔ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :-ከግንቦት 7 ጋር በማበር መፈንቅለ መንግስት ልታደርጉ ነው በሚል ምክንያት ከሚያዚያ 16 ቀን 2001 .. ጀምሮ እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ላለፉት ስምንት ዓመታት በጨለማ እስር ቤት ውስጥ ሰቆቃ ሲፈጸምባቸው የቆዩት ጄነራል ተፈራ ማሞና ጄነራል አሳምነው ጽጌ እስርቤት ውስጥ ተንቀሳቃሽ ስልክ አስገብታችኋል በሚል ምክንያት በደረሰባቸው አሰቃቂ ድብደባ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው እራሳቸውን በመሳታቸው ሆስፒታል ገብተዋል። በተጨማሪም የጄኔራል አሳምነው ጽጌ አክስት 14 ዓመት ልጃቸው ጋር ለአንድ ቀን ታስረው ከሕግ ውጪ ምርመራ ተደርጎባቸዋል። ከጄኔራሎቹ ጋር አብሮ የታሰረ አንድ የኦሮሞኛ ቋንቋ ጋዜጠኛም በጨለማ ክፍል ውስጥ ታስሮ አሰቃቂ የሆነ ድብደባ እየተፈጸመበት መሆኑንምንጮችአስታውቀዋል። ጄኔራሎቹና አብረዋቸው የተከሰሱት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ላይ እጃቸው ከተያዘበት እለት ጀምሮ ዓይናቸው በጨርቅ እየተሸፈነ አካላዊ ጥቃቶች ሲፈጸምባቸው እንደቆየ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወቃል። ከተከሳሹቹ አብዛሃኞቹ ካለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በህወሃት ልዩ የደኅንነት ኃይሎች በምርመራ ሰበብ በየጊዜው ልብሳቸውን እያወለቁ ከመገረፋቸውም በላይ እስካሁን ድረስ ሕጋዊ መብታቸው ሳይከበር በጨለማ ቤት ተጥለው ከቤተሰቦቻቸው፣ ከጠበቆቻቸውና ከሰብዓዊ መብት ተሟጓቾችጋር እንዳይገናኙ ተደርገዋል።

No comments: