Monday, June 20, 2016

በረሃብ አድማ ላይ የሚገኘው አቶ አግባው ሰጠኝ በብሄሩ የተነሳ ስቃይ እየደረሰበት መሆኑን ተናገረ

ሰኔ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- በእነ ጌታቸው መኮንን መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው 1 አመት 8 ወራት ላላነሰ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙት 16 ተከሳሾች ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ከእነሱ መካከል አቶ አግባው ሰጠኝ በማንነቱ የተነሳ ስቃይ እየደረሰበት መሆኑን ገልጿል። አቶ አግባው ከግንቦት 17 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ በቂሊንጦ ጨለማ ቤት ውስጥ ታስሮ የሚገኝ ሲሆን፣ በጀመረው የረሃብ አድማ ለአንድ ሳምንት ያክል ምግብ አለመመገቡ ታውቋል። አግባው አማራ በመሆኔ በደል እየተፈጸመብኝ ነው ያለ ሲሆን፣ የእስር ቤቱ ሃላፊዎችዘረኛ ብለህናልበማለት እያሰቃዩት መሆኑን ገልጿል። አግባው በፍርድ ቤቱ ፊትዘረኛነታችሁ ሀቅ ነውሲል ተናግሯል። 16 ተከሳሾች ናቸው። ከታሰሩ 1 አመት 8 ወር ሆናቸው። ዛሬ ይከላከሉ ወይስ በነጻ ይሰናበቱ በሚለው ላይ ይወስናሉ ቢባልም አልደረሰም በሚል ለሰኔ 21 ቀጠሮ ተሰጣቸው። ተከሳሾች ሁሉም ከአማራ ክልል የመጡ ናቸው። የፓርቲዎች የዞን አመራሮች ነበሩ። በተለያየ ጊዜ በማንነታቸው ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤት ተናግረዋል። አካላዊ ጉስቁልና የከፍተኛ የሰውነት መደካም የሚታይበት አግባውቤተሰቤንና ጠበቃዬን እንዳላይ ካልተደረገ በረሃብ አድማው እቀጥልበታለሁ፣ ቀጣይ ቀጠሮ ላይ ሬሳዬ ሊመጣ ይችላልብሎአል። 16 ተከሳሾች ይከላከሉ ወይስ በነጻ ይሰናበቱ በሚለው ላይ የፍርድ ቤት ውሳኔ ያገኛሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ ፍርድ ቤቱ ውሳኔው አልደረሰም በሚል ለሰኔ 21 ቀጠሮ ሰጥቷል። ሁለቱም ተከሳሾች የሰማያዊ እና የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የአካባቢ አመራሮች የነበሩ ናቸው።

No comments: