Monday, June 6, 2016

አርበኞች ግንቦት7 በአውሮፓ የተሳካ የድጋፍ ማሰባሰብ ስራዎችን ሰራ

ግንቦት ፳፱(ሃያ ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :-የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ በኖረዌይ ኦስሎ ቅዳሜ ባዘጋጀው ዝግጅት የአርበኞች ግንቦት 7 /መንበር / ብርሃኑ ነጋ እና / ጌታቸው በጋሻው በእንግድነት ተገኝተዋል።  ከፍተኛ ህዝባዊ የትግል ስሜት በተነጸባረቀበት በዚህ መድረግ፣  ከስዊዲን ፊንላንድ ዴንማርክ  እና ከሌሎችም  የአውሮፓ ሃገሮች የመጡ ኢትዮጵያውያን ተካፍለዋል።

በዝግጅቱ 800 000 የኖርዌጂያን ክሮነር በላይ ገቢ መገኘቱንም ለማወቅ ተችሎአል።

በስዊዘርላንድም እንዲሁ / ብርሃኑ ነጋ በተገኙበት የተሳካ የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ተካሂዷል። የሁለቱ ዝግጅቶች ሂደት ፋይል እንደደረሰን ዝርዝር ሪፖርት የምናቀርብ መሆኑን ለመግልጽ እንወዳለን።



No comments: