Monday, May 9, 2016

ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት መረጃ በማቀበል ወንጀል ተከሰሱ

ሚያዚያ (ግንቦት) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- የፌደራሉ አቃቤ ህግ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14 ወንጀል ችሎት ምክትል አስር አለቃ አጃናው ታደሰና ምክትል አስር አለቃ ቻሌ ነጋ ላይ ለአርበኞች ግንቦት7 ወታደራዊ መረጃዎችን ሲያቀብሉ ነበር የሚል ክስ ተከፍቶባቸዋል።
ሁለቱ ተከሳሾች 6 እና 25 ክፍለ ጦር ስር የሚገኙ ሬጅመንቶችን ብዛት እና መገኛ ቦታ በስልክና በቫይበር ማስተላለፋቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።
ተከሳሾቹ የአገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የገቡትን ቃል ኪዳን ወደ ኋላ በመተውና የአርበኞች ግንቦት ሰባት ድርጅትን ተልዕኮ በመቀበል፣ የመከላከያ ሠራዊትን አደረጃጀትና የሚገኝበትን አድራሻ መረጃ አሳልፈው በመስጠት፣ ከድርጅቱ ታጣቂዎች ጋር ለመቀላቀልና የድርጅቱ ተስፋ በመሆን በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው ተዘግቧል። ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ለማዬት ግንቦት 15 ቀን 2008 .. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

No comments: