Thursday, May 26, 2016

ኢኮኖሚው ሰራዊቱን ሊሸከመው አልቻለም ተባለ

ግንቦት ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ሰራዊቱን ሊሸከመው አለመቻሉ የኢህአዴግ 25 አመታት የመከላከያ አስተዳደር በሚገመገምበት ወቅት መነሳቱ ታውቛል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ የሰራዊቱን ፍላጎት ማሙዋላት አለመቻሉ በሰራዊቱ ውስጥ እየተባባሰ ለመጣው ችግር ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።
የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት በስብስቡ እና አመራሩ በነባር ታጋዮች የተያዘ እና በጦር ካምፕ ብቻ ተነጥሎ የሚኖር ሰራዊት በመሆኑ ህዝባዊነት አልተላበሰም የሚል ትችት ቀርቦበታል። ሰራዊቱ ሙሉ በሙሉ ኢህአዴግዊ ባህርይ አለመላበሱም በውይይቱ ተገልጿል።

No comments: