Wednesday, May 18, 2016

ከዘረኛና አምባገነን ስርዓት ለመላቀቅ ሁሉም ዜጎች ትግሉን እንዲቀላቀሉ በእስር የምትገኘው እየሩሳሌም ተስፋው ጥሪ አቀረበች

ኢሳት (ግንቦት 10 2008)
ነጻ ለመውጣት የመጀመሪያው ራስን ከታሰሩበት የፍርሃት እስር ነጻ በመውጣት ትግሉን መቀላቀል ነውስትል የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባልና በሽብር ወንጀል ክስ በእስር ላይ የምትገኘው እየሩሳሌም ተስፋው ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት በጻፈችው ደብዳቤ ገለጸች።
እየሩሳሌም ይህንን ደብዳቤ ግንቦት 7 1997 ምክንያት በማድረግ ለህዝብ እንዲደርስ የፈለገችው ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች በእለቱ ለህዝብ አለመድረሱ በጽሁፉ ተገልጿል።
እየሩሳሌም በጽሁፏ በግንቦት 7 1997 የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነቱ ያደረገውን ተሳትፎ እና እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት ሰጥታለች።
ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ያልተማረረ ዜጋ አይገኝም ሁሉም ነጻነትን ይናፍቃል፥ ነጻ ለመውጣት ግን ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ይፈራልያለችው እየሩሳሌም፣ ገዢው ህወሃትን ለማስወገድና ህዝባዊ መንግስት ለመመስረት ሁሉም መረባረብ እንዳለበት አትታለች።
ስትቀጥልም በተለይ ግንቦት 1977 ለብዙዎች ሞት፣ አካል መጉደልና፣ እስራት አብቅታለች መራራው ሳያልፍ ጣፋጭ፣ ሳይሞክሩ ትንሳዔ የለምና በባለፈው ከመጸጸት ያለፈው እልህ አሲዞን ይህንን ዘረኛና አምባገነን የሽፍታ ቡድን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መንግለን ለመጣል እንዘጋጅ ስትል ጥሪ አቅርባለች።
በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ መዝገብ አርበኞች ግንቦት 7 ለመቀላቀል ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል ክስ በእስር ላይ የምትገኘው እየሩሳሌም፣ አቶ በቅርቡ ባሰራጨችው ጽሁፍ አንዳርጋቸው ጽጌን አንስታለች።
የነጻነት ታጋዩ ጀግናው አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር አንድ ግቢ ውስጥ ብንኖርም፣ መገናኘት አልቻልንም በማለትየአንተ መታፈን ትግሉን አያሽመደመደውም፣ ይበልጥ አጦዘው እንጂ። ለእኛ ከቤት መውጣት ምክንያት አንተ ነህ እኛ የአንተ ፍሬዎች ነንስትል አቶ አንዳርጋቸው የከፈለውን መስዋዕትነት ጠቅሳለች።


No comments: